#Ethiopia | በዓለም ዙሪያ በጉጉት የሚጠበቀው 23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ውድድር መጀመሩን በማበሰር፣ ታዋቂው የለስላሳ መጠጥ አምራች ኮካ ኮላ ያዘጋጀው ልዩ የምረቃ ምሽት ትላንት ማታ ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስካይላይት ሆቴል በታላቅ ድምቀት ተከናውኗል።
በዚህ ልዩ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የክብር እንግዶችና ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች፣ በሜክሲኮ እና በደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የተደረገውን እጅግ አጓጊ የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ጨዋታ ከዲኤስቲቪ ጋር በመተባበር በተዘጋጀ ግዙፍ ስክሪን ላይ በጋራ ተከታትለዋል።
ከዓለም ዋንጫ ውድድሮች ጋር ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለቀ የረጅም ጊዜ አጋርነት ያለው ኮካ ኮላ ያሰናዳው ይህ የምሽት ዝግጅት፣ የስፖርት አፍቃሪያንን እና ልዩ እንግዶችን በታላቅ እግር ኳሳዊ ስሜት ያገናኘ ነበር።
ከተጠባበቀው የመክፈቻ ጨዋታ በተጨማሪም፣ በስነ ሥርዓቱ ላይ የታደሙት እንግዶች በተለያዩ አዝናኝ ስፖርታዊ ውድድሮች፣ ማራኪ የሙዚቃ ትዕይንቶች እና ልዩ ልዩ የመዝናኛ መርሃ ግብሮች ምሽቱን በደስታና በፈገግታ አሳልፈውታል።
#WorldCup2026 #CocaCola #FIFAWorldCup #DStvEthiopia #FootballFamily #SportEntertainment #SkylightHotel #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen








No comments yet.