ታርጋ ለመቀየር የጊዜ ሰሌዳ ይወጣል‼️
ነባር ተሽከርካሪዎች አዲሱን ሰሌዳ የሚቀይሩት በሚወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መሆኑ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘገየ በላይነህ፣ አዲሱን የተሽከርካሪ ሰሌዳ አተገባበር አስመልክቶ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም የአገልግሎት አሰጣጡን ሂደትና ለነባር ተሽከርካሪዎች የተዘጋጀውን አቅጣጫ ይፋ አድርገዋል።
በሥራ ላይ ያሉ ነባር ተሽከርካሪዎች አዲሱን ሰሌዳ የሚቀይሩት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት መሆኑን ገልጸዋል።
አዲሱ ስማርት ሰሌዳ በአሁኑ ወቅት እየተሰጠ ያለው የተሸከርካሪ ታርጋ ለመዉሰድ ተመዝግበዉ በመጠባበቅ ላይ ላሉ እና ከዚህ በሁዋላ አዲስ ለሚመዘገቡ ተሽከርካሪዎች መሆኑን ገልጸዉ ፤ ተመዝግበው ሰሌዳ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ ተገልጋዮች እንግልትና የጊዜ መባከን እንዳይኖር፣ ቀደም ሲል በተመዘገቡበት ቅደም-ተከተል መሠረት ከየቅርንጫፎቹ ጥሪ ሲደረግላቸዉ መጥተው አገልግሎቱን እንደሚወስዱ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
#አዲሱ_ስማርት_ሰሌዳ
ከተሽከርካሪው ዕድሜ ጋር እኩል የሚዘልቅ (Durability)፦ ሰሌዳው ጠንካራና የረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ፣ ተሽከርካሪው የአገልግሎት ለውጥ በሚያደርግበት ጊዜ የማይቀየርና ተጨማሪ ወጪን ሙሉ በሙሉ የሚያስቀር ነው።
ከፍተኛ የደህንነት ጥንቃቄ የተደረገበት በመሆኑ ማጭበርበር ይከላከላል።
ሰሌዳው ዘመናዊ ቺፕና የፊት መስታወት ላይ የሚለጠፍ የRFID መለያ አብሮት ያለው በመሆኑ፣ የተሽከርካሪውን አሁናዊ መረጃ (Real-time data) በሰከንዶች ውስጥ ለማወቅ ያስችላል።
ሰሌዳዉ በቪየና ኮንቬንሽን መሠረት ለሀገራችን የተሰጠውን ዓለም አቀፍ የ “ETH” ኮድ ይዟል።

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.