ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለሩዋንዳ የ250 ሚሊዮን ዶላር የብድር አገልግሎት ፈቀደ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የሩዋንዳ መንግስት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሁኔታዎች መጥበቅ ጋር ተያይዞ የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እና የማህበራዊና የልማት ወጪዎቹን ለመጠበቅ ያቀረበውን የ250 ሚሊዮን ዶላር አዲስ የተራዘመ የብድር አገልግሎት ጥያቄ በስራ አስፈፃሚ ቦርዱ ማጽደቁን አስታወቀ።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ መሰረት፣ ብድሩ ለ38 ወራት የሚቆይ ሲሆን ቦርዱ ስምምነቱን ማጽደቁን ተከትሎ የ35.7 ሚሊዮን ዶላር የመጀመሪያ ዙር ክፍያ ወዲያውኑ እንዲለቀቅ ፈቅዷል።

የሩዋንዳ የኢኮኖሚ እድገት እ.ኤ.አ. በ2025 9.4 በመቶ የደረሰ ቢሆንም፣ በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ጦርነት ግን የሀገሪቱን እድገት እ.ኤ.አ. በ2026 ከ6.8 በመቶ በታች ያወርደዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአይኤምኤፍ መግለጫ አመልክቷል። በጦርነቱ ምክንያት በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ እና የማዳበሪያ ዋጋ መጨመሩ በሀገሪቱ ላይ የዋጋ ንረትን እና የበጀት ጫናን እየፈጠረ መሆኑም ተጠቅሷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu
#ቅዳሜገበያ#etbusinessview
#Ethiopia#IMF #Rwanda


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1