#Ethiopia | የተስፋ አዲስ ልጆቻቸውን በካንሰር ያጡ ወላጆች እና በጎ ፈቃደኞች፣ ህክምናው ተደራሽ እንዲሆን በማሰብ ከዛሬ 14 ዓመት በፊት የጀመሩት የበጎ አድራጎት ነው። ዋናው ግቡም ልጆቻቸውን ለማሳከም በብዙ የህክምና ውጣ ውረድ ውስጥ ያለፉ ወላጆች፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን ለመርዳት በማሰብ ነው። ምንም አይነት ገቢ ወይም ሃብት ያልነበረው ይህ ተስፋ አዲስ፣ በትናንሽ ነገሮች ነበር ጅማሮውን ያደረገው ። ከዚያም ቀስ በቀስ በማደግ፣ አሁን ወደ ሰባት ሆስፒታሎች የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
ታዲያ ይህን አገልገሎት ይበልጥ ለማስፋት ይረዳ ዘንድ ፣ “ተስፋ አዲስ” የበጎ አድራጎት ድርጅት ከአራራይ ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ እና የደም ልገሳ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።
የአራራይ ፕሮሞሽን ስራ አስኪያጅ ፣ ወጣት ክብሮም ሃብቱ (ጆን)፣ የካንሰር ታማሚ ህፃናት ህክምና ብዙ ደም እንደሚጠይቅ ገልፀው፣ ህብረተሰቡ ደም በመለገስ እና በሩጫው በመሳተፍ ለህፃናቱ ተስፋ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል። የፕሮግራሙ ብራንድ አምባሳደር የሆነው ቲክቶከር ቅዱስ አማኑኤልም፣ ተከታዮቹ በዚህ ቅዱስ ዓላማ ላይ ከጎኑ እንዲቆሙ እና ደም በመለገስ ለህፃናቱ እንዲደርሱ ጥሪውን አስተላልፏል።
የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫው አስተባባሪ እና የአራራይ ፕሮሞሽን ምክትል ስራስካያጅ፣ ወጣት መሃመድ ንጉስ እንደገለፀው፣ ሩጫው የሚካሄደው ሐምሌ 12 /2018 ዓ.ም ሲሆን መነሻው አትላስ አደባባይ ፤በውሃ ልማት አድርጎ መዳረሻውን አትላስ አደባባይ ያደርጋል።
ለሩጫው የሚሆኑ ቲሸርቶች በተስፋ አዲስ የካንሰር ህፃናት ድርጅት ይገኛሉ።
ለበለጠ መረጃ፡
መሐመድ፡ 0920875941
ጆን፡ 0914777751
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen









No comments yet.