የፕላስቲክ መክተፊያና ተያያዥ ስጋቶችበየቀኑ በኩሽናችን ውስጥ የምንጠቀምባቸው የፕላስቲክ መክተፊያዎች (Cutting Boards)…

- Advertisement -
Sidebar AD
የፕላስቲክ መክተፊያና ተያያዥ ስጋቶች‼️
በየቀኑ በኩሽናችን ውስጥ የምንጠቀምባቸው የፕላስቲክ መክተፊያዎች (Cutting Boards) አብዛኞቹ ከፖሊኢቲሊን (Polyethylene) ወይም ፖሊፕሮፒሊን (Polypropylene) የተሰሩ ናቸው።
እነዚህ መክተፊያዎች ምግብ ስንከትፍ በሚፈጠር ግጭትና ጭረት ምክንያት በዓይን የማይታዩ ጥቃቅን የፕላስቲክ ቅንጣቶች (Microplastics) ወደ ምግባችን እንዲቀላቀሉ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።
የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ የፕላስቲክ መክተፊያዎችን አዘውትሮ መጠቀም በዓመት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጥቃቅን የፕላስቲክ ቅንጣቶችን ወደ ሰውነታችን እንዲገቡ ሊያደርግ ይችላል።
መክተፊያው ባረጀና በቢላዋ ጭረት በበዛበት ቁጥር የሚወጣው የፕላስቲክ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።
ምንም እንኳን ወደ ሰውነታችን የሚገባው የፕላስቲክ መጠን ትክክለኛ ክብደት ላይ አሁንም ጥናቶች ቢቀጥሉም፣ ቅንጣቶቹ ወደ ደም ዝውውር የመቀላቀልና በረጅም ጊዜ ለጤና ስጋት የመሆን እድላቸው ግን አሳሳቢ ነው።
ይህ ሁኔታ በተለይ በህጻናት ላይ ጥንቃቄን ይሻል። ህጻናት እያደጉ ያሉ በመሆናቸውና የሰውነት ክብደታቸው አነስተኛ በመሆኑ፣ ወደ ሰውነታቸው የሚገቡ የኬሚካል ቅንጣቶች ከአዋቂዎች ይልቅ በእድገታቸውና በሆርሞን ስርዓታቸው ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ።
ማይክሮ ፕላስቲኮች ወደ ሰውነት ከገቡ በኋላ የሚከተሉትን ችግሮች ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ስጋቶች አሉ፦
1. በፕላስቲክ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች (እንደ BPA ያሉ) የተፈጥሮ ሆርሞኖችን ስራ ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ።
2. ጥቃቅን ቅንጣቶቹ በሴሎች ውስጥ በመከማቸት ለተለያዩ ብግነቶች መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ።
3. ፕላስቲኮች ሌሎች አካባቢያዊ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ስበው የመያዝ ባህሪ ስላላቸው ተጨማሪ ስጋት ይፈጥራሉ።
መፍትሄው :-
1. የእንጨት መክተፊያዎችን መጠቀም የእንጨት መክተፊያዎች ከተፈጥሮ (Cellulose) የተሰሩ በመሆናቸውና የመቆረጥ እድላቸው ዝቅተኛ በመሆኑ ተመራጭ ናቸው።
2. ያረጁ መክተፊያዎችን መቀየር የፕላስቲክ መክተፊያ የሚጠቀሙ ከሆነ ጥልቅ ጭረቶች ሲፈጠሩና ሲያረጅ በአዲስ መቀየር ያስፈልጋል።
3. ጥንቃቄ በተለይ በሆቴሎችና በስጋ ቤቶች ውስጥ ትልልቅ ቢላዎችና መጥረቢያዎች ስለሚጠቀሙ፣ መክተፊያዎቹ ላይ የሚፈጠሩ ጥልቅ ጭረቶች ለፕላስቲክ ቅንጣቶች መለቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው።
ጤናችንን ለመጠበቅ የለት ተለት ልምዶቻችንን ቆም ብለን ማጤንና የተሻሉ አማራጮችን መከተል ለነገው ደህንነታችን ወሳኝ ነው።
ይህ መረጃ ለሌሎችም ጠቃሚ ነው ብለው ካመኑ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ያካፍሉት (Share ያድርጉ)።”
Via ፍላቴ ጣሳው

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: