የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ከወዲሁ ታወቀ? የጀርመናዊው ሊቅ አስገራሚ ግምት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ባለፉት ሦስት ተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች የጀርመንን፣ የፈረንሳይን እንዲሁም የአርጀንቲናን ድል አስቀድሞ በትክክል በመተንበይ ስሙ ናኝቶ የቆየው ምጣኔ ሀብት አዋቂና የሂሳብ ሊቅ ዮአኪም ክሌመንት ለዘንድሮው የዓለም ዋንጫ አዲስ መላምት ይዞ ብቅ ብሏል።

ባለሙያው የስፖርታዊ ብቃትን መለኪያዎች ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነ-ህዝባዊ መረጃዎችን ያካተተ ሳይንሳዊ የስሌት ቀመር በመጠቀም በ2026ቱ ታላቅ የኳስ መድረክ ኔዘርላንድስ ባለድል እንደምትሆን አስታውቋል።

ይህ የክሌመንት አዲስ መግለጫ እንደ አርጀንቲና፣ ፈረንሳይ፣ እንግሊዝ እና ስፔን ላሉት ግዙፍ የኳስ ሀገራት የተሰጠውን ቅድሚያ ግምት ወደ ጎን በመግፋት ለሆላንድ እውቅና በመስጠቱ በስፖርቱ ማህበረሰብ ዘንድ ሰፊ መነጋገሪያ ፈጥሯል።

በሊቁ ሳይንሳዊ ቀመር ትንተና መሰረት በሮናልድ ኪውማን የሚመራው የኔዘርላንድስ ብሔራዊ ቡድን ለፍጻሜ ደርሶ የፖርቹጋልን አቻ በመርታት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ሻምፒዮንነትን ክብር ይቀዳጃል።

እግር ኳስ ሁልጊዜም ባልተጠበቁ ክስተቶችና በአጋጣሚዎች የተሞላ በመሆኑ ስሌቱ መቶ በመቶ ፍጹም ሊሆን እንደማይችል ባለሙያው ቢያስገነዝብም፣ ከዚህ ቀደም በ1974፣ 1978 እና 2010 ለፍጻሜ ደርሰው ለጥቂት ዋንጫው ያመለጣቸው ብርቱካናማዎቹ ከአንድ ወር በኋላ በሚጠናቀቀው በዚህ ውድድር ታሪክ ሰርተው ግምቱን እውን ካደረጉት፣ የጀርመናዊው ምሁር የማይሳሳት የትንበያ ስም በዓለም መድረክ ላይ በድጋሚ ደምቆ የሚመዘገብ ይሆናል።#አዲስ አድማስ

#WorldCup2026 #Netherlands #JoachimKlement #FootballPrediction #WorldCupWinners #Football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: