በደራሲ ቢያብብ መለሰ
#Ethiopia | ለምን አልጠየቅንሕም ?
አንተስ ለምን አልነገርከንም ? ምናልባት
” ምራቅ ዋጥ ስታደርጉ ይደርሳችኋል” ብለሕ አስበሕልን ይሆን ?
ጥያቄውን ተነቦ በማይጠገብ ግለ ታሪኩ ” ” መጽሐፍ ላበረከተልን የቀድሞ የአቃቂ አድቬንቲስት መምሕራችን ቢያብብ መለሰ ምስጋናችን በተማሪዎችሕ ስም ይድረስ።
መጽሐፉን ለጊዜው እዚያው አቃቂ አድቬንቲስት ትምሕርት ቤት ታገኙታላችሁ በርቀት ላላችሁ በሌላ አማራጮች እናሳውቃለን ።
መልካም ንባብ!!
***
“እኔን አሰቃይታችሁ የምታገኙት ምንድነው? ሶስታችሁም ሽጉጥ አላችሁ። ሽጉጣቹ ጥይት የለውም ? እንደዚሕ ከምታሰቃዩኝ በጥይት ብትገሉኝ ምንአለበት ?” አላቸው እነሱም ከጥቂት ቀናት ቡሐላ ከቁስሉ ላይ ሲደበድቡት ሊዘረግፍላቸው እንደሚችል ዝተው ደጋግፈው አንስተው ያወለቀውን ሱሪ አስታጥቀው ከክፍሉ አስወጡት።
ኮለኔሉ የልቡ ስላልደረሰ በቁጭት ከንፈሩን ነከሰ ። ተማሪው የማባዣ ክፍሉ ሰራተኛ እንደሰጡት ቢናገርም ኮለኔሉ ግን እኔ እንድደበደብ ትእዛዝ ሰጠ ። ትእዛዙን ለመፈጸም ዝግጁ ሆነው ሚጠብቁት ገራፊዎች “ተማሪው እኮ ሰጠኝ ያለው የማባዣ ክፍሉን ነው” ለማለት ድፍረት ስላልነበራቸው በቅጽበት አስረው አንጠለጠሉኝ።
ከባለታሪኩ መጽሐፍ የተወሰደ
***
የታሪኩ የአጻጻፍ ስልት ፣ የሐሳብ ፍሰትና የቃላት አጠቀቀም የጸሐፈውን የስነ-ጽሑፍ ልዩ ችሎታና ብቃት ያረጋግጣሉ። ይህ ደፋ ቀና የበዛበት የሕይወት ጎዳና ሕልም/ቅዝት ወይሞ ልብ ወለድ ድርሰት ላይ ተሞርክዞ የተሠራ ፌልም እንጂ፣ ባለታሪኩን ለማያውቅ ሰው ዕውነተኛ የሕይወት ገጠመኝ ነው ብሎ ለመቀበል እጅግ ያዳግታል። …
አንጂነር ፀጋዓለም ያለው
… በሕይወቱ በሙሉ ያየቸውንና የተጋፈጣቸውን ችግሮችና ሁኔታዎች የቀረበበት የአጻጻፍ ስልት ይበል የሚያሰኝ ነው። ባሳለፋቸው ሥርዓተ መንግሥታት በሀገራችን ያየቸውንና የሰማቸውን ምስቅልቅሎች በጣፋጭ ቃላት አሳምሮ ደስታዎቹ በሳቅ እንዲያስፈነደቁ፣ ችግሮቹ በለቅሶ እንዲያንፈቀፍቁ አድርጎ ለአንባቢያን እንካችሁ ብሏል።…
አቶ ፈጠነ ትዕዛዙ
… በታሪኩ ውስጥ ያሉትን ክንዋኔዎችና ድርጊቶች ለመግለጽ የተደረገው ጥንቃቄ በሳልነት የተሞላበት በመሆኑ የሚደነቅ ነው። በጥቅሉ በታሪኩ ውስጥ የተንፀባረቁት ጉዳዮችና ድርጊቶች በጸሐፌው ታሪክ መልክ ይቅረቡ እንጂ በአመዛኙ የሁሉ አቀፍነት ባህርይ ስላላቸው አእንባቢው የኣቸው ጠቀሜታ የጎላ ይሆናል የሚል ግምት አለኝ።…
ዶክተር የሺጥላ ሀብተማሪያም
…ግለ ታሪክ የአካባቢ ከዚያም አልፎ የሀገር ታሪክ አካል መሆን እንደሚችል ይህ መጽሐፍ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ለምሳሌ ዘመናዊ ትምህርት፣ ዕድገት በኅብረት የዕውቀትና የሥራ ዘመቻ እና ብሔራዊ ውትድርና በመጽሐፋ ውስጥ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ ኩነቶ ደግሞ የሀገራችን ታሪክ አካል ናቸው፡፡…
ዶክተር ፈንታሁን አየለ
…መልካም ትውልድን ለማስቀጠል የእናቶችን አና የአባቶችን ራስን አሳልፎ የመስጠት ጽነ ፍቅር ሽጋ በሆኑ ቃላት ከትቦታል። ‘ጋሻ’ የሚለው ነባር ቃል ክብደቱ እና ጥልቀቱ እንዲሁም ጥቅሙ የገባኝ ጸሐፌው ወንድሙና ሌሎች ቤተሰቦቹ ተወላዲያነን እንዴት እንደሚታደን ነቃሽ አቅርቦ ሲያሳየኝ ነው:: በዚህም ያልተበጠሰ ብዙ ሰብዓዊ ገመድ እናያለን፤ ስሌሎች የመኖር እሴትን።
እቶ ምህረት ዳኜው
#Biography #EthiopianLiterature #NewBook #ReadingCulture #AkakiAdventist #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.