ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው በመንከባከብ፣ በመርዳትና በመደገፍ ላይ የሚገኘው አዲስ ጀማሪ ድርጅት የምስረታ

- Advertisement -
Sidebar AD

ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ህፃናትና ቤተሰቦቻቸው በመንከባከብ፣ በመርዳትና በመደገፍ ላይ የሚገኘው አዲስ ጀማሪ ድርጅት የምስረታ በአሉን አከበረ።

#Ethiopia | በኢትዮጵያ የተቸገሩ ህጻናትና ቤተሰቦቻቸው አቅም በመፍጠር፣ በመደገፍ እና ህይወታቸውን በመለወጥ ረገድ እየሰራ የሚገኘው “አዲስ ጀማሪ” ድርጅት 10ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ አክብሯል።

በፈረንጆቹ በ2016 የተቋቋመው ድርጅቱ፣ ባለፉት አስር ዓመታት ህጻናትን ከቤተሰቦቻቸው ጋር በማቀናጀትና በማቆየት፣ የትምህርት ድጋፍ በማድረግ፣ ስልጠናዎችን በመስጠት እንዲሁም ቤተሰቦችን በኢኮኖሚ የማብቃት ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

በችግር ውስጥ ያሉ ህጻናት ተንከባካቢ ቤተሰብ እንዲያገኙ በማድረግ፣ ወደ ማህበረሰቡ ተመልሰው የተሻለ ህይወት እንዲመሩ ሲያግዝ ቆይቷል።

ቤተሰቦች ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን እንዲሰሩ በማድረግ፣ ህጻናት ከቤተሰቦቻቸው ሳይለዩ ተገቢውን ድጋፍ አግኝተው እንዲያድጉ ስራዎችን ሲሰራ እንደነበር ተገልጿል።

የድርጅቱ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሲንዲ ዳግላስ (Cindy Douglass) በበዓሉ ላይ እንደተናገሩት፣ ባለፉት አስር ዓመታት ድርጅቱ ለብዙ ህጻናትና ቤተሰቦች የተስፋ ብርሃን መሆን ተችሏል ብለዋል።

“በእያንዳንዱ ቤት እና ቤተሰብ ውስጥ የተፈጠረው ለውጥ ትልቅ ምስክር ነው” ያሉት ስራ አስኪያጇ በቀጣይም ቤተሰቦችን በማብቃት የተሻለ ህይወት እንዲመሩ ለማድረግ ድርጅታቸው በትጋት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ህይወትን የመለወጥ እና ተስፋ መገንባት በሚል10ኛ ዓመት የምስረታ በአሉን ያከበረው ድርጅቱ ለዚህ መድረሳችን በሁሉም እገዛ ምክንያት ነው ብለዋል።

በበዓሉ ላይ የመንግስት ተወካዮች የሌሎች አጋር ድርጅቶች ተወካዮች፣ የድርጅቱ ሰራተኞች እና ተጠቃሚዎች የተገኙ ሲሆን፣ ባለፉት አስር ዓመታት በድርጅቱ ታሪክ ውስጥ ከድርሻ ለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጥቷል።

ድርጅቱ በቀጣዮቹ አስር ዓመታት ጉዞውም፣ የተጎዱ ህጻናትንና ቤተሰቦቻቸውን በማገዝ የላቀ ውጤት ለማምጣት ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

#አዲስጀማሪድርጅት #በጎአድራጎት
#ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen #Mediacommunication





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: