የአሮሞ አንድነት መሰረቱ ገዳ ነው!

- Advertisement -
Sidebar AD

– የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ

#Ethiopia | በዛሬው እለት በተከናወነው 71ኛው የገዳ ቱለማ የስልጣን ሽግግር ስነ ስርዓት ላይ ገዳ ሜልባ ስልጣኑን ለገዳ ሚቺሌ በይፋ አስረክቧል።

በዚህ ታሪካዊ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንደተናገሩት፥ ህዝቡ በተለያዩ ጊዜያት ያጋጠሙትን በርካታ ተጽዕኖዎች በጽናት በመቋቋም የራሱን ማንነት፣ ባህልና መልካም እሴቶች ጠብቆ ማቆየት ችሏል።

ባለፉት ዘመናት የገጠሙትን ጫናዎች በሙሉ አልፎ የማንነቱ መገለጫ የሆነውን የገዳ ስርዓት በጉያው በመያዝ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር ማድረጉንም ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት ስርዓቱ የሚገባውን ስፍራ አግኝቶ እንዲመለስ የባህል ተሃድሶ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የጠቆሙት አቶ ሽመልስ፤ የኦሮሞ ባህልና እሴት በጠንካራ መሰረት ላይ ተገንብቶ እንዲለማ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ህብረትና አንድነት መሰረቱ የገዳ ስርዓት መሆኑን ያረጋገጡት ፕሬዚዳንቱ፤ ይህንን እሴት ይበልጥ ማፅናትና የሁልጊዜም መመሪያ ማድረግ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

#OBN #መስፍን በቀለ

#Oromia #GedaSystem #GedaTulema #ShimelisAbdisa #Culture #EthiopianCulture #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1