ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረ ተሽከርካሪ በደረሰ አደጋ የ28 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታውቋል።
አደጋው የደረሰው ከደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች መካከል በሚገኘው የሐረጎ መንገድ ላይ ነው።
ዛሬ ሰኔ 08/10/18ዓ.ም ማለዳ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረ የሕዝብ አውቶቡስ በተለምዶ ሐረጎ እየተባለ በሚጠራው መንገድ ላይ በደረሠበት አደጋ እስካሁን የ28 ሰው ሕይወት ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባተቸዋል።
የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው በግምት100 ሜትር ጥልቀት ወዳለው ገደል ገብቶ ነው አደጋው የደረሠው። በሕይወት የተረፉትን ወደ ሕክምና ቦታ ለማድረስ አሁንም ርብርብ እየተደረገ መኾኑን የገለጸው ፓሊስ የአደጋውን ምክንያት በመጣራት ላይ መኾኑን አስታውቋል።












No comments yet.