የመላእክት ቅዱስ ሚካኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃ እና ረድኤቱም አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል፡፡ ከመጀመሪያው ሰው አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አምነው ለሚጠሩት ረዳት ነው፡፡ በመዝሙር 33÷7 እደተጻፈው ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል፡፡ እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል፡፡ የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው፡፡ ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል እንደተናገረው ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው፡፡ ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን ድንቅ ተአምር መስከረም ዘጠኝ ቀን መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን ትመሰክራለች፡፡ በቀድሞው የሮም ግዛት ‘ሩፍምያ’ የምትባል ከተማ ነበረች፡፡

ይህች ከተማ በእምነታቸው ጠንካሮች የሆኑ ጥቂት ክርስቲያኖችና በርካታ ኢአማንያን ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት፡፡ በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ፍጹም የእምነት ሰው ነበር፡፡ በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረግ ስለነበር ተበለጥን የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ “ዮናናውያን”ይሕንን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ፡፡ በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን መከሩና ወሰኑ፡፡ በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ አለ፡፡ በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር፡፡ ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ ዘግተው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት ከቀናት በኋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ፡፡
ወንዙ ትልቅ ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ፡፡ በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ ቤተ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በስተቀር ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ሲወጣ ወንዙ እየደነፋ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው፡፡ ከደቂቃዎች በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ እንደሚሆን የተረዳው መጋቢ በታላቅ ድንግጤ ውስጥ ወደቀ፡፡ እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ በመላዕክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስዕል ፊት ወድቆ ተማጸነ፡፡ ታላቁ ወንዝ ቤተ ክርስቲያኑን ጠርጎ የሚወወስደው ከሆነም የሚሆነውን ነገር ለመቀበልና ከዚያም ላለመውጣትም ወሰነ፡፡ ትንሽ ቆይቶ በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ፡፡ በዚህ ጊዜ የመላዕክት ሁሉ አለቃቸው ለጠራውም ፈጥኖ የሚደርሰው ቅዱስ ሚካኤል በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ፡፡

መጋቢውንም “ጽና አትፍራ፣ እኔ ካንተ ጋር ነኝና” ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት፡፡ በዚያች ቅጽበትም ትልቅ ሸለቆ ተፈጠረ፡፡ በአስፈሪ ሁኔታ ሲመጣ የነበረው ወንዝም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ፡፡ የሚገርመው ነገር የመላዕክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሸለቆው የተፈጠረው ከቤተ ክርስቲያኑ በታች መሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያኑ ግን ጸንቶ ቆመ፡፡ መጋቢውም እግዚአብሔርንና ቅዱስ ሚካኤልን አመሰገነ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ፡፡ በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው፣ መልአኩንም አከበሩት፡፡
ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያስገዙ ገዳማውያንና ቅዱሳን ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እየደገፍን በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2