ሕወሓትን የተቃወሙት የ76 አመት አዛውንት ታሰሩ‼️
በትግራይ ክልል የእንደርታ ተወላጅ የሆኑት የ76 ዓመቷ ነባር ታጋይ አኸዛ ሕሉፍ፣ በክልሉ ስላለው የፍትህ እጦት፣ የመልካም አስተዳደር እክል እና የፖለቲካ ብልሽት አስመልክተው ከሶስት ቀናት በፊት የሰጡት ቃለመጠይቅ መነጋገሪያ መሆኑን ተከትሎ በህወሓት ታጣቂዎች ታግተው መታሰራቸው ተሰማ።
የወረዳ 70 እንደርታ የፈለግማያት ጣቢያ ነዋሪ የሆኑት እናት ለምን ተነፈስሽ? ለምንስ ተናገርሽ?” በሚል ዛሬ መታሰራቸውን ተረጋግጧል። እንደ መረጃዎች ገለጻ ለእስራታቸው ዋነኛ ምክንያት የሆነው “ለምን ልጆች ወደ ጦርነት ይገባሉ?” በማለት ሰላማዊ ጥሪ ማቅረባቸውና እንደሌሎቹ የጦርነት ነጋሪት ለመጎሰም ፈቃደኛ አለመሆናቸው ሲሆን፣ የቀድሞው ህወሓት እስከ እድሜ ልክ የሚያስቀጣ አፋኝ ህግ ማውጣቱ በሚታወስበት በዚህ ወቅት የ76 ዓመት አዛውንት በአመለካከታቸው ማሰሩ ከፍተኛ ቁጣንና ትዝብትን እየቀሰቀሰ ይገኛል።
እስካሁንም እናት አኸዛ ሕሉፍ በታጣቂዎች ተወስደው የት ቦታ እንደታሰሩና አሁን ያሉበት ሁኔታ በትክክል አለመታወቁ ተገልጿል።
@Seledadotio

No comments yet.