የኢትዮጵያ አሰልጣኞች ማህበር ምርጫ ህገ-ወጥ ነበር

- Advertisement -
Sidebar AD

✍በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ

#Ethiopia | በኢትዮጵያ አሰልጣኞች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ የተካሄደው የአመራር ምርጫ ከህግና ከማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ውጪ ተፈጽሟል ሲሉ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ አስገራሚ ይፋዊ አስተያየት ሰጥተዋል።

ሻምበል ቶሎሳ እንደገለጹት፣ በምርጫው ሂደት ወቅት ከመተዳደሪያ ደንብ ውጪ የተፈጸሙ አካሄዶች መኖራቸውን ለጉባኤው ለማሳወቅ ሞክረዋል።

“እኔ ማድረግ የምችለው ነገር ይህ ሂደት ከህግ ውጪ እየተካሄደ መሆኑን ለጠቅላላ ጉባኤው ማሳወቅ ብቻ ነበር፤ ይህ አካሄድ ትክክል አይደለም ብዬ ተናግሬ ነበር” ብለዋል።

እንደ ገለጻቸው፣ በዚህ ወቅት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተወከሉት ባለሙያ በሚያስገርም ሁኔታ ጠቅላላ ጉባኤው ይወስን የሚል የተሳሳተ ሀሳብ በማንሳታቸው ከመተዳደሪያ ደንብ ውጪ እውቅና የሌላቸው ክልሎች ድምፅ እንዲሰጡ ተደርጓል።
“ያንን ሂደት ማገድ አልቻልኩም።

በመጨረሻም ምርጫው ተካሄደ፣ ህጉ ተሽሮ የአሰልጣኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ተመረጠ” ሲሉ ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ አስረድተዋል።

ይህ ጉዳይ በማህበሩ ውስጥ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጣልቃ ገብነት የተፈጠረውን ውዝግብ በቀጣይ በኢትዮጵያ የስፖርት አስተዳደር ውስጥ ህጋዊነት፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ዙሪያ አዲስ ውይይት ሊያስነሳ የሚችል ሲሆን፣ በማህበሩ ውስጥ የተፈጠረው ውዝግብ ቀጣይ እንዴት እንደሚፈታ ትኩረት ስቧል።

👉 ሻምበል ቶሎሳ ቆቱ ከጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ ጋር በቻናል 1 ስፖርት ፕሮግራም ያደረጉትን ሙሉ ቆይታ ዕለተ አርብ ምሽት 3:00 ሰዓት በቻናል 1 ቴሌቪዥን እና በቻናል 1 የዩቲዩብ ገጽ ይከታተሉ።

​#የኢትዮጵያአሰልጣኞችማህበር #ሻምበልቶሎሳቆቱ #ስፖርት #አትሌቲክስፌዴሬሽን #የስፖርትአስተዳደር #ቻናል1ስፖርት #ጌጡተመስገን #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa #getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2