ረዳት ፕሮፌሰር እና ሠዓሊ ልዑል ሣኅለማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ውስጥ ለረጅም ዘመናት በሥነጥበብ መምህርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ታዋቂው ሰዓሊና ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ታውቋል።

ረዳት ፕሮፌሰር ልዑል ሣኅለማርያም በሀገራችን ዘመናዊ የሥነጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ካሳረፉ ታዋቂ ሰዓልያን መካከል አንዱ ሲሆኑ የፖይንት ግሩፕ የሥነጥበብ ስብስብ መሥራችና አባልም ነበሩ።

ባለፉት ሦስት አስርት ዓመታት በትምህርት ቤቱ ውስጥ በረዳት ፕሮፌሰርነትና በትምህርት ክፍል ኃላፊነት በመሥራት በርካታ ተተኪ የጥበብ ባለሙያዎችን ያፈሩ ተወዳጅ መምህር ነበሩ።

በተጨማሪም በትምህርት ቤቱ አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ትልቅ አስተዋጽዖ ያበረከቱ ጠንካራ ሙያተኛ እንደነበሩ ይነገራል።

ታዋቂው የጥበብ ሰው ልዑል ሣኅለማርያም በሙያዊ ብቃታቸው ብቻ ሳይሆን በማኅበራዊ ሕይወት ተሳትፏቸው፣ በደግነታቸውና በሰው ወዳድነታቸው በብዙዎች ዘንድ የተመሰገኑ ነበሩ።

የሥነጥበብ ሥራዎቻቸውንም በሀገር ውስጥና በተለያዩ የውጭ ሀገራት በግልና በቡድን ለዕይታ በማቅረብ ትልቅ ስም ያተረፉ ባለሙያ ናቸው።

የደራሽ የጥበብ ሰው የቀብር ሥነሥርዓት ረቡዕ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ በ9 ሰዓት እንደሚፈጸም ታውቋል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የጥበብ ማኅበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን።

ነፍስ ይማር።

#AleSchoolofFineArtsandDesign #AddisAbabaUniversity #EthiopianArt #LeulSahlemaryam #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: