ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ እና ፋሜ ባይ ሺራዝ የሀገርን ገጽታ በጥቅል ለማስተዋወቅ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲጂታል ሚዲያና ብራንድ ማስተዋወቅ ላይ የሚንቀሳቀሰው ፋሜ ባይ ሺራዝ የተሰኘው ተቋም የሀገርን ገጽታ የመገንባት ስራ ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን በጋራ ገለጹ።

የዚሁ ዓለም አቀፍ ተቋም መስራች የሆኑት ሺራዝ ሀሰን እና የስራ ባልደረቦቻቸው በፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ ተገኝተው የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎንም ከሚዲያው የማኔጅመንት አመራሮች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ዘርፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ተቋማት ያላቸውን ልምድና የዲጂታል ሚዲያ አቅም በማስተባበር፣ በሀገር ገጽታ ግንባታ ስራዎች ላይ ተቀናጅተው ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ይህ ትብብር የሀገርን ገጽታ የማስተዋወቅ ተግባራትን በዘመናዊና ስልታዊ በሆኑ የዲጂታል መንገዶች በተደራጀ መልኩ ለመደገፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#DigitalMedia #BrandPromotion #TourismEthiopia #MediaPartnership #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: