ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ አዲስ ጥቃት ሊከፍት ተዘጋጅቷል በማለት ከሠሠ። መንግሥት የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም፣ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ሕወሃት፣ ፌደራል መንግሥቱ በትግራይ ላይ አዲስ ጥቃት ሊከፍት ተዘጋጅቷል በማለት ከሠሠ።
መንግሥት የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም፣ ጦር ሠራዊቱን በማነቃነቅና በትግራይ ላይ እቀባ በማድረግ ሁለተኛ ዙር ጦርነት ሊያካሂድ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ያለው ሕወሃት፣ የፌደራል መንግስትቱ ባለስልጣናት የትግራይ ኃይሎችን በጦርነት ሰባኪነት የሚከሱት የጦርነት ዝግጅታቸውን አቅጣጫ ለማስቀየር ነው በማለት ተችቷል።
በትግራይ ስላለው ሁኔታ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን ሕዝብና ዓለማቀፉን ማኅበረሰብ እያሳሳቱ ይገኛሉ በማለት ጭምር ሕወሃት ወቅሷል።
ሕወሃት፣ ባለፉት ሦስት ወራት ለጦርነቱ ተፈናቃዮች ይቀርብ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ መቋረጡንም ገልጧል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2