በትግራይ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች አሰቃቂ እርምጃ እየወሰዱ ነው!
ቢቢሲ ትግረኛ በትግራይ ክልል እየተፈጸመ ስላለው የግዳጅ ወታደራዊ አፈሳ አስደንጋጭ የምርመራ ሪፖርት ይዦ ወጥቷል፡፡ በወርቅ ማውጫ ስፍራዎች እና በሌሎች ስፍራዎች እየተፈጸመ ያለውን አፈሳ በዝርዝር የሚዳስሰው ዘገባው፤ ከህውሃት ታጣቂዎች ባለፈ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎችም በንጹሃን ላይ እርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኝ ጠቅሷል፡፡ እነዚህ ጭምብል ያጠለቁ ታጣቂዎች የሕውሓት ወታደሮች ስለመሆናቸው ግን አልታወቀም፡፡
ግንቦት 17/2018 ዓ.ም. በዓብይ ዓዲ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ሁለት የወርቅ ማዕድን ማውጫዎች አባግባ እና ሩባኸዛ ከሚባሉ አካባቢዎች የትግራይ ኃይሎች አርሚ 60 አባላት እና ፊታቸውን የሸፈኑ ታጣቂዎች ከ700 ሰዎች በላይ ሰዎችን እንዳፈሱ ቢቢሲ ትግርኛ ከተጎጂዎች እና ከተጎጂ ቤተሰቦች መረጃ አግኝቷል።
የአራት ልጆች አባት የሆነው አቶ ሰለሞን ኃይለማርያም በዓብይ ዓዲ ከተማ ለሌሎች ሰዎች ድንጋይ እና አሸዋ በአህያ በመሸከም የቀን የጉልበት ሥራ ሠርቶ በሚያገኘው ገንዘብ ልጆቹን ያሳድግ ነበር። ነገር ግን እንደተለመደው ለሥራ ከወጣ በኋላ ከዛ በኋላ እሱ እና የአጎቱ ልጅ ወደ ቤት ሳይመለሱ መቅረታቸውን ቤተሰቡ ለቢቢሲ ገልጿል።
ባለቤቱ ወይዘሮ መድረኽ ኪዳነማርያም “ሰኞ ዕለት ወደ ሥራ እንደሄደ ጥዋት 3፡00 ሰዓት ላይ ነው ወሰዱት።. . . የምሠራበት ቦታ መንገድ ዳር ስለሆነ በግዳጅ ታፍሰው በመኪና ሲያልፉ አየሁኝ። ‘እዚህ መኪና ላይ አለ’ ሲሉኝ 500 ብር ተበድሬ ስጡልኝ ብየ ሰጥኋቸው” ብላለች።
ከዚያም በኋላ ባለቤቷ ከማይቅነጣል አልፎ ወደሚገኝ ወታደራዊ ማሠልጠኛ እንደተወሰደ መረጃ እንዳገኘችም ትገልፃለች። “በጣም ተጨንቀናል። ልጆቹ ናፍቀውታል። አባታችን እያሉ እያስቸገሩኝ ነው። ልጆቹን የሚረዳ አንድም የለም። ሰለሞንም ልጆቹን ትቶ እዚህ ውስጥ የመግባት ፍላጎት የለውም፤ በኃይል ነው የወሰዱት።”
ዘካርያስ* ከወርቅ ማውጫ አካባቢ “ፊታቸውን በሸፈኑ ታጣቂዎች” በኃይል ከታፈሱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች መካከል አንዱ ነው።
በአፈሳው ወቅት ድብደባ፣ ማንገላታት እና ተኩስ ጭምር እንደነበር የሚናገረው ዘካሪያስ ከጣንቋ አበርገለ፣ ቀይሕ ተኽሊ እና ዓብይ ዓዲ ወረዳዎች የመጡ 500 ሰዎች ወደ ዓብይ ዓዲ ከተማ ማዘጋጃ ቤት፤ ከቆላ ተምቤን የመጡ 200 ሰዎች ደግሞ በዓብይ ዓዲ ከተማ ነዳጅ ማደያ አቅራቢያ ወደሚገኘው ግንባታው ወዳላለቀ ሕንፃ በታጣቂዎቹ መወሰዳቸውን ይናገራል።
ቢቢሲ ትግርኛ ያነጋገራቸው ሌሎች ሰዎች ከታፈሱ በኋላ ለከተማው ፖሊስ እና ፀጥታ አካላት እንዲሁም ለዓብይ ዓዲ ከተማ እና ወረዳ አስተዳደር እንዳስረከቧቸው ይናገራሉ።
በዓብይ ዓዲ ከተማ ማዘጋጃቤት አዳራሽ የከተማዋ ከንቲባ እና ምክትሉ እንዲሁም የፀጥታ ኃላፊዎች በመምጣት ‘ትዋጋላችሁ’ እንዳሏቸው ጨምረው አስረድተዋል።
ከማዕድን ቁፋሮ የተያዙት ወጣቶች ” ‘ወድ ትግል ነው የምትሄዱት’ አሉን። ልብስ ሳንለብስ ራቁታችን ነን ያለነው፣ እቃችን እና ሞባይላችን ሳንይዝ ከሥራ ላይ ነው ያፈሳችሁን፤ ልብሳችንን እንኳን እንልበስ አልናቸው። እነሱ ግን ‘አያገባንም አትሄዱም አሉን” ብለዋል።
ዘካሪያስ በተለያየ ጊዜ በትግራይ ውስጥ በተካሄደ ጦርነት የቤተሰቡ አባላቱ መሰዋታቸውን ገልጾ ከተጣራ በኋላ መለቀቁን ተናግሯል።
ከዚያም በኋላ አውቶቡስ፣ ኦራል እና አይሱዙ መኪኖች አምጥተው ጭነው ወደ ሌላ ቦታ እንደወሰዷቸው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ተጎጂዎች ይናገራሉ።
የአርሚ 60 የትግራይ ኃይሎች ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ዘልዑል ማቲዮስ ለቢቢሲ በሰጡት ምላሽ የሚመሩት ቡድን በአባግባ አካባቢ ተሰማርቶ “እርምጃ” እንደወሰደ ገልጸዋል።
“በአካባቢው ሰፊ የማዕድን ወረራ አለ። እዚያ የነበሩትን ወጣቶች ‘ኦፕሬሽን’ በማካሄድ በትነናቸዋል። . . . በሩባኸዛ እና በአባግባ የነበረ ወጣት ለሌላ የፀጥታ ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ስለነበር እርምጃ ወስደናል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ወጣቶቹ ማይቅነጣል እና ዕዳጋ ዓርቢ መካከል ወደሚገኘው ወታደራዊ ማሠልጠኛ እንደተወሰዱ ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ ኮሎኔሉ “… የማውቀው ነገር የለም” ሲሉ መልሰዋል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.