#FastMereja | የክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች መሥራችና ፕሬዝዳንት ነቢይ ኢዩ ጩፋ፣ በሥነ-መለኮት (Theology) የትምህርት ዘርፍ የማስተርስ ዲግሪያቸውን ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. እንደሚቀበሉ ተገለጸ።
የምረቃ መርሐ ግብሩ መጀመሪያ በ2017 ዓ.ም. መግቢያ ተይዞ የነበረ ቢሆንም፣ የነቢዩ እናት ህልፈተ ህይወትን ተከትሎ ጥያቄ ቀርቦ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን የኮሌጁ ምክትል ፕሬዝዳንት ገልጿል፣ ጥያቄው ተቀባይነት አግኝቶ መርሐ ግብሩ ለሰኔ 14 ተቀጥሯል።
በሌላ በኩል ነቢይ ኢዩ ጩፋ የዶክትሬት (PhD) ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ጥናታቸውን አጠናቀው በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እንደሚቀበሉ ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
Source: FastMereja









No comments yet.