ወላይታ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ
ከወላይታ ሶዶ ወደ ገሳ ከተማ 50 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ “ዛሮ ቁልቁለት” ኤልፋ በተባለ አስቸጋሪ መንገድ ላይ ተገልብጧል።
በአደጋው የ4 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፣ በ22 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ24 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን እንደገለፀው፣ ተጎጂዎች ወደ ህክምና ተቋማት ተወስደዋል።
ይሁን እንጂ በደረሰው የጉዳት መጠን ምክንያት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልፇል።
የአካባቢው አስቸጋሪ መልክዓ ምድር ለክስተቱ መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ የተጠቆመ ሲሆን፣ ፖሊስ ስለ አደጋው ዝርዝር ምርመራ እያደረገ ይገኛል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.