የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳደግና ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትርክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ ተመ

- Advertisement -
Sidebar AD

የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳደግና ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትርክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) ጋር በመተባበር የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማሳደግና ዲጅታል ኢትዮጵያን 2030 እውን ለማድረግ የሚያስችል የኤሌክትርክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያ አስመርቆ ለአገልግሎት ዝግጁ አድርጓል፡፡

በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ተቋሙ ውጤታማ የአሰራር ስርዓትን በመዘርጋትና የደንበኞችን እርካታ ለማሳደግ በርካታ ዘመናዊ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው በተለይም የሀገራችንን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ ለማሳለጥና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የበኩሉን ታሪካዊ ሚና እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡

አክለውም በመጀመሪያው ምዕራፍ በአዲስ አበባ ከተማ በበጀት ዓመቱ መጋቢት ወር ስራ ከጀመሩት የኮተቤ፣ የልቡ እና የፒያሳ የኃይል መሙያ ጣቢያዎች በተጨማሪ፤ ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን (IPDC) ጋር በመተባበር በአንድ ጊዜ ለ24 መኪኖች አገልግሎት መስጠት የሚችል እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ የኃይል መሙያ ጣቢያ ግንባታን አጠናቆ ዛሬ በይፋ መመረቁን አብስረዋል።

ይህ ስራ በአዲስ አበባ ብቻ የሚገደብ አይደለም ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው በቅርብ ወራት ውስጥ በቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ ባቱ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ እና ሐዋሳ ከተሞች ላይ የሚገነቡት የኤሌክትሪክ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናሉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር ዶ/ር ፍሰሀ ይታገሱ በበኩላቸው የተመረቀው የኢቪ (EV) ቻርጅ ስቴሽን በሀገሪቱ የማኑፋክቸሪንግ ጉዞ ላይ ትልቅና ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይህንን ታሳቢ በማድረግ ላከናወነው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማሳደግ የተቋሙ መለያ (ሎጎ) የሆነው «ኢኮ ኢንዱስትሪያል ፓርክ» ከዚሁ የቻርጅ ስቴሽን ስራ ጋር ትልቅ እንድምታና ቁርኝት እንዳለው በመጠቆም፣ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው ግንኙነት እጅግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢፌዴሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር አቶ በረኦ ሀሰን በበኩላቸው በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መካከል ያለው ትብብር የሀገሪቱን መጻኢ ዕድል ለመወሰን እጅግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የኢቪ (EV) ቻርጅ ስቴሽን ሥራ ለትራንስፖርት ዘርፉ ትልቅ መሠረት እንደሆነ የጠቆሙት ሚኒስትር ዲኤታው፣ በአሁኑ ሰዓት እንዲህ ያሉ የቻርጂንግ ስቴሽኖችን ማብዛትና በትኩረት መስራት ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ልማት ጉዞ የሰጠችውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

አያይዘውም፣ የአየር ንብረት ለውጥን (ክላይሜት ቼንጅ) ለመከላከልና የአረንጓዴ አሻራ (ግሪን ሌጋሲ) ውጥኖችን ለማስቀጠል በዚህ ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ዋነኛውና ቁልፍ ስራ መሆኑን በመግለጽ፣ በዚህ አስደሳችና ተስፋ ሰጪ ስራ ውስጥ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ሙሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች ቁጥር 140 ሺህ የደረሰ ሲሆን ተቋሙ በመጀመሪያው ምዕራፍ በአዲስ አበባ 32 እንዲሁም በሌሎች ከተሞች 8 በድምሩ 40 የቻርጂንግ ጣቢያዎች ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

ከኢቪ (EV) ቻርጅ ስቴሽን ምረቃው ጎን ለጎን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ ውስጥ የችግኝ ተከላ ስራ መርሃ ግብርም ተካሂዷል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: