ጊፍት ሪል ስቴት በአዲስ አበባ ለገሃር መንደር አዳዲስ ፕሮጀክቶቹን አስተዋወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​ጊፍት ሪል ስቴት በለገሃር መንደር ባዘጋጀው ልዩ የቤት ሽያጭ ኤክስፖ ላይ እየሰራ ያለውን የተለያዩ ፕሮጀክቶቹን በይፋ አስተዋውቋል።

‎ጊፍት ሪል ስቴት በኤክስፖው ላይ ደንበኞቹን የሚስቡ የተለያዩ የቤት ባለቤትነት አማራጮችን እና የዋጋ ቅናሾችን ይፋ አድርጓል።

‎​በዚህ የቤት ሽያጭ ኤክስፖ ላይ ከቀረቡት ልዩ አማራጮች መካከል ተጠቃሚዎች ሙሉ ክፍያ ሳይጠብቁ የፈለጉትን ቤት በሁለት በመቶ ቅድመ ክፍያ ብቻ እንዲይዙ የሚያስችል ዕድል ይገኝበታል።

‎በተጨማሪም ድርጅቱ ለደንበኞቹ እስከ አርባ አምስት በመቶ የሚደርስ የባንክ ብድር የማመቻቸት ስራ እንደሚሰራ ገልጿል።

‎ከዚህም ባሻገር እንደ ግንባታው ሂደት እስከ አስራ ስምንት በመቶ የሚደርስ የታላቅ ዋጋ ቅናሽ የተደረገ ሲሆን፣ በአንድ ጊዜ ሙሉ ክፍያ ለሚፈጽሙ ደንበኞች ከስምንት እስከ አስራ ስምንት በመቶ ቅናሽ ከተጨማሪ የዋጋ ንረት መከላከያ ዋስትና ጋር ተዘጋጅቷል።

‎ለፈጣን ባለቤትነት በሚል በተዘጋጀው የሁለተኛ ፓኬጅ አማራጭ ደግሞ፣ ዘጠና አምስት በመቶ የደረሱ ግንባታዎችን በሃያ አምስት በመቶ ቅድመ ክፍያ ብቻ የቤት ባለቤት የመሆን ዕድል ተመቻችቷል።

‎​ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በዘርፉ ታማኝነትን ያካበተው ጊፍት ሪል ስቴት፣ በአዲስ አበባ መሃል ከተማ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ሃያ ሁለት ማዞሪያ፣ ሲኤምሲ፣ አትላስ እና ለገሃር ባሉ ዋና ዋና ቦታዎች ዘመናዊ ቪላዎችን፣ አፓርትመንቶችን እና የንግድ ሱቆችን ገንብቶ እያስረከበ መሆኑን በኤክስፖው ላይ ተገልጿል።

📷 ከበደ መክብብ
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: