የኢኳቶሪያል ጊኒ መንግሥት ሥልጣን መልቀቁ ተነገረ

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢኳቶሪያል ጊኒ መንግሥት አላሳካሁም ባላቸው ግቦቹ ምክንያት ሥልጣን መልቀቁ ተነገረ። የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ልጅ የሆኑት ምክትል ፕሬዝደንት ቴዎዶሮ ንጉማ ኦቢያንግ ማንጌ ትናንት ይፋ እንዳደረጉት የኢኳቶሪያል ጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር የመንግሥት ባለሥልጣናትን የመልቀቂያ ደብዳቤ አቅርበዋል። ምክንያታቸው የመንግሥት ካቢኔ ከግብ ለማድረስ ካቀዳቸው እስካሁን ያሳካው 10 በመቶ ብቻ ነው የሚል ነው። እንዲያም ሆኖ መንግሥት ሊያሳካ አቅዶ እስካሁን አልሆነለትም የተባለው ምን እንደሆነ ግልጽ አለመደረጉን ሮይተርስ አመልክቷል።

የኢኳቶሪያል ዴሞክራቲክ ገዢ ፓርቲ (ፒዲጄ) መግለጫ እንዳመለከተው መንግሥት በሥልጣን ላይ በነበረበት ወቅት እንደ የመንግ|ሥት አስተዳደር፣ የመሠረተ ልማት፣ የመንግሥት አገልግሎቶች እና የኢኮኖሚ ልማት ባሉ ዘርፎች የተለያዩ ተነሳሽነቶችን ተግባራዊ አድርጓል።
የመንግሥት ባለሥልጣናት የጋራ ሥራቸውን መልቀቅም የመንግሥትን መዋቅርን በማሻሻል ለታሰቡ አዳዲስ ቅድሚያ የሚሰጣቸው በየጊዜው የሚከናወኑ የተቋማዊ መልሶ ማደራጀት ሂደቶች አካል ነው ሲል ፓርቲው በፌስቡክ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝደንት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ንጉማ ምባሶጎ ከጎርጎሪዮሳዊው 1979 ዓ,ም ጀምሮ ሥልጣን እንደያዙ ነው። ይህም በዓለማችን ለረዥም ዓመታት በሥልጣን የሰነበቱ ፕሬዝደንት ያደርጋቸዋል። ልጃቸውም ምክትላቸው ሆኖ ኤኳቶሪያል ጊኒን በቤተሰብ እየመሩ ነው።

DW Amharic


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: