REALITY PIAZZA PALACE VIEW PROJECT
በዘመናዊ ቴክኖሎጂና ከፍተኛ የጥራት መስፈርት እየተገነባ ነው!
#Ethiopia | ሪያሊቲ ሪል እስቴት “ሪያሊቲ ይለያል – THE DIFFERENCE IS IN DETAILS” በሚለው መርሁ የሚታወቀው ድርጅት፣ በአዲስ አበባ የታሪክ፣ የንግድ እና የመዝናኛ ማዕከላት በሆኑ ቦታዎች አቅራቢያ የሚገኘውን “ሪያሊቲ ፒያዛ ፓላስ ቪው” ፕሮጀክት በዘመናዊ የአርክቴክቸር ዲዛይንና ዘላቂ የኑሮ ፅንሰ ሀሳብ እያለማ መሆኑን የሪያሊቲ ሪል እስቴት ባለቤትና CEO አቶ ዮሐንስ ገመዳ አስታወቁ።
አቶ ዮሐንስ አያይዘው እንደተናገሩት ፕሮጀክቱ በ4,000 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የሚገነባ ሲሆን ከ70,000 ሜትር ኪዩብ ወይም 16 ሜትር ( አራት ቤዝመንት) በላይ የቁፋሮ ሥራ ተከናውኗል። በድርጅቱ የፋይናንስ አቅም ፕሮጀክቱን 300 ሚሊዮን ብር በማውጣት መጠነሰፊ ሰፊና የመሠረት ሥራዎቹ በብቃት መጠናቀቃቸውን አስረድተዋል።
ፕሮጀክቱ በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል የሚገኝ ሲሆን፣ ከአድዋ ሙዚየም 853 ሜትር፣ ከቸርችል ጎዳና 465 ሜትር፣ ከፍሬንድሺፕ ፓርክ 240 ሜትር፣ ከዩኒቲ ፓርክ 770 ሜትር እንዲሁም ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 955 ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ አቶ ፍጹም ገብሩ የኮንስትራክሽ ቺፍ ኮንስትራክሰሸ ኦፕሬሽኝ ኦፊሰር
ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ከሼራተን ሆቴል እና ከሊሴ ገብረ ማርያም ትምህርት ቤት አቅራቢያ መገኘቱ ለነዋሪዎችና ለባለሀብቶች ልዩ የቦታ ጥቅም እንደሚሰጥ አቶ ፍጹም አብራርተዋል።
የ“ፖላስ ቪው” ፕሮጀክቱ በቴክኒካል ጥራት፣ በዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂ እና በከተማ ገጽታ ላይ በሚያመጣው አዎንታዊ ተፅዕኖ ተለይቶ የሚታይ ፕሮጀክት ነው ያሉት ደግሞ ቴክኒካል ማናጀሩ አቶ ዳርዮስ ፍቃዱ ናቸው።
በፕሮጀክቱ ውስጥ አራት ቤዝመንቶች የታቀዱ ሲሆን፣ 8 ሜትር ስፓን ያላቸው የኮለም አቀማመጦች እና 7 በመቶ የራምፕ ተዳፋት በመጠቀም ሰፊና ምቹ የፓርኪንግ ሥርዓት እንዲኖር መደረጉ ገልጸዋል።
እንዲሁም 10 ሊፍቶች እና 4 የአደጋ መውጫ ደረጃዎች የታቀዱ ሲሆን፣ ሕንጻው የእሳት ደህንነት መስፈርቶችን በሙሉ የሚያሟላ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል።
በሜካኒካል፣ ኤሌክትሪካል እና ሳኒተሪ ሥርዓቶች ዘርፍም የኤሌክትሪክ እና የሳኒተሪ ዳክቶች ለየብቻቸው መዘጋጀታቸው፣ ዘመናዊ የካሜራና የኢንተርኮም ሥርዓት መካተቱ እና በቂ የአየር ዝውውር የሚያቀርብ የሜካኒካል ቬንቲሌሽን ሲስተም መዘርጋቱ ተጠቅሷል።
የሪያሊቲ ሪል እስቴት ባለቤትና CEO አቶ ዮሐንስ ገመዳ ፕሮጀክቱ በዘመናዊው Post-Tension (PT) Slab System ቴክኖሎጂ የተቀየሰ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህም ሰፊ ስፓን ለመፍጠር፣ የግንባታ ፍጥነትን ለማሳደግ እና የስትራክቸር ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችል መሆኑ ገልጸዋል።
ከከተማ ገጽታ አንፃርም፣ ሕንጻዎቹ ከ5ኛ ወለል ጀምሮ በመንታ ቅርጽ የሚይዙ ሲሆን ለአካባቢው ዘመናዊ የአርክቴክቸር ገጽታ እንደሚያበረክቱ አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ሰፊ የአረንጓዴ ልማት፣ በዛፎች የተሸፈነ ቴራስ እና ሁለቱን ሕንጻዎች የሚያገናኝ ድልድይ ለፕሮጀክቱ ልዩ የውበት እሴት እንደሚጨምሩ ጠቁመዋል።
ሪያሊቲ ሪል እስቴት ፖላስ ቪው ፕሮጀክት ለመኖሪያ ቤት ፍላጎት መፍትሔ ከመስጠቱ ባሻገር ለከተማው አዲስ ገጽታ የሚያበረክት፣ የዘመናዊ ግንባታ መለኪያ የሚሆን እና የድርጅቱን የጥራት ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ፕሮጀክት ነው።****
ዘመናዊ የኑሮ ፍላጎቶችን በማሟላት 24 ሰዓት የጥበቃ አገልግሎት፣ ስታንድባይ ጄኔሬተር፣ ሰፊ ፓርኪንግ፣ የቆሻሻ ማስወገጃ ሥርዓት፣ ዘመናዊ ሊፍቶች፣ ጂምናዚየም፣ የመቀበያ አዳራሽ፣ ባለብዙ ዓላማ አዳራሽ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መሙያ ጣቢያዎች እና የውጭ አትክልት ስፍራዎችን ያካትታል።
የመኖሪያ እና የንግድ አገልግሎቶች መግቢያዎች ለየብቻ ናቸው። ከመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎቶች አንፃርም ከ200 በላይ ሱቆች፣ ከ1 እስከ 3 መኝታ ቤት ያላቸው አፓርታማዎች፣ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ ሰፊ የፓርኪንግ ቦታዎች እና በሩፍቶፕ የመዝናኛ ስፍራዎችን ይዟል።
የሪያሊቲ ሪል እስቴት የማርኬቲንግ ዳይሬተር
አቶ ሙሉቀን ሽፈራው እንደተናገሩት “መሸጥ ማስረከብ አይደለም። እኛ – (ሪያሊቲ ሪል እስቴት) ግን የሸጥነውን እያስረከብን ነው። … ማስረከብ ተክነንበታል። ይህ የደንበኞቻችን የምስክርነት ድምፅ ነው” ብለዋል።
አቶ ሙሉቀን ሪያሊቲ ሪል እስቴት ለአንድ ሳምንት የሚቆይ ልዩ የንግድ ኤክስፖ ይዘን መጥተናል። ለ 30 ቤቶችን ብቻ በ 90,200 ብር እንዲሁም በ 102 ሺህ ብር ደግሞ የተለያዩ ቤቶችን ለሽያጭ አቅርበናል። ይህ በ48 ወራት የሚጠናቀው ለቤት ፈላጊዎች ትልቅ የምሥራች፤ ትልቅ ዜና ነው”ብለዋል።
“ሰማችን እውነት ነው፣ ሥራችንም የእውነት ነው – DELIVERING THE TRUTH ” በሚል መርህ የሚሰራው ሪያሊቲ ሪል እስቴት፣ ይህ ፕሮጀክት ዘመናዊ አርክቴክቸር፣ ዘላቂ የኑሮ ዘይቤ እና ምርጥ የቦታ ምርጫን በአንድ ላይ ያጣመረ የልህቀት ምሳሌ፤ መሪ ኩባንያ ( Leading Company ) ሆኖ እየሠራ፤ እየታተረ ይገኛል።
በ10 ዓመታት የሪል እስቴት ጉዞ 14 ፕሮጀክቶቾ፤ በ2018ዓም 4 ፕሮጀክቶች የሪያሊቲ ሪል እስቴት ሕያው ቋሚ ሥራዎቹ ናቸው።
ይህ ሪያሊቲ ሪል እስቴት ጉዞ ይቀጥላል …
“ሪያሊቲ ይለያል!
– THE DIFFERENCE IS IN DETAILS”
+251-977-292929
+251-948-233333



Source: GetuTemesgen









No comments yet.