ባለፈው ሳምንት አርብ ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ “አቧራው ጨሰ” የተሰኘውን ቴአትር ለማየት አቅንተን ነበር፣ ሲኒማ ቤት ከገባው

- Advertisement -
Sidebar AD

ባለፈው ሳምንት አርብ ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ “አቧራው ጨሰ” የተሰኘውን ቴአትር ለማየት አቅንተን ነበር፣ ሲኒማ ቤት ከገባው ስለቆየው ሰልፍ ይጠብቀኛል ብዬ አልጠበኩም ነበር 11:30 ስደርስ ህዝቡ ሰልፉን ይዞ ቲኬት እየቆረጠ ይገባል።

ቲኬታችን ይዘን 12:00 ሰዓት ወደ ውስጥ ገባን በነገራችን ቲኬት ስንቆርጥ የመቀመጫ ቦታው በዛው መምረጥ እንችላለን፣ እንደድሮ ዝም ብሎ ያገኙት ቦታ መቀመጥ የለም።

አዳራሹ ቀስበቀስ ሞልቶ ፈሰሰ፣ ህዝቡ ለካ አለም ሲኒማ እየገባ ነው መንገድ ላይ የማይታየው፣ ተጠባቂው ቴአትር መጋረጃው ተገልጦ ተጀመረ፣ “አቧራው ጨሰ” የወጣቱን ህይወት የሚዳስስ የቤት ኪራይ፣ ትዳር፣ ስደት በሳቅ ፍርስ እያደረገ የሚዳስስ ምርጥ ቴአትር ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ)፣ ብስራት ሱራፌል፣ ቃልኪዳን ታምሩ፣ ቅድስት ገ/ስላሴ በድንቅ ትወና አስደምመው አስጨብጭበውናል።

እለት አርብ ቦሌ ዓለም ሲኒማ በ12:00 ሰዓት ለተመልካች እየቀረበ ይገኛል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: