የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የዋንጫ ድርቅ፤

- Advertisement -
Sidebar AD

የሃሪ ኬን ታሪካዊ የግብ ክብረ ወሰን

#Ethiopia | የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ብቸኛውን የዓለም ዋንጫ ካነሳ ስድስት አሥርት ዓመታት ቢቆጠሩም የአውሮፓ ዋንጫን ግን አንዴም ማሸነፍ አልቻለም።

ይህች የእግር ኳስ ማዕከል የሆነች ሀገር እንደ ተፅዕኖዋ የዋንጫ ባለቤት አለመሆኗ ብዙዎችን ቢያስገርምም ታሪክ የማይዘነጋቸውን በርካታ ከዋክብት ለዓለም አበርክታለች። ከእነዚህም መካከል እንደ ሃሪ ኬን ያለ ምሉዕ የፊት መስመር አጥቂ ማግኘቷ ልዩ ያደርጋታል።

በሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም ሆትስፐር 281 ግቦችን ቢያስቆጥርም በዋንጫ ባለመታደሉ ወደ ጀርመኑ ባየር ሙኒክ አምርቶ ሦስት ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል።

ሆኖም በክለብ ደረጃ ውጤታማ ቢሆንም የብሔራዊ ቡድን መንገዱ ግን አሁንም ዋንጫ አልባ ሆኖ ቀጥሏል። የሦስቱ አናብስት ስኬት በዋንጫ ባይደገፍም ትላንት ምሽት በተደረገው 23ኛው የዓለም ዋንጫ እንግሊዝ ክሮሺያን 4 ለ 2 በረታችበት ጨዋታ ሃሪ ኬን ሁለት ግቦች አስቆጥሮ የእንግሊዝን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን ይበልጥ አርቆ ሰቅሎታል።

በዓለም ዋንጫም 10 ግቦችን በማስቆጠር ከየትኛውም እንግሊዛዊ ተጫዋች ልቋል።

በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ2026 የዓለም ዋንጫ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ በዳላስ ስታዲየም የተደረገ ሲሆን የባየርን ሙኒኩ አጥቂ ሃሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምትና በጨዋታ ያስቆጠራቸው ሁለት ግቦች በዓለም ዋንጫ ያስቆጠረውን አጠቃላይ የግብ መጠን 10 በማድረስ የቀድሞውን ኮከብ ጋሪ ሊንከርን ክብረ ወሰን ለመጋራት አስችሎታል።

ጁድ ቤሊንግሃም እና ተቀይሮ የገባው ማርከስ ራሽፎርድ ቀሪዎቹን ግቦች ሲያስቆጥሩ የክሮሺያን ግቦች ማርቲን ባቱሪና እና ፔታር ሙሳ አስቆጥረዋል።

ምድብ 12 ላይ የምትገኘው እንግሊዝ በቀጣይ ጋናን የምትገጥም ሲሆን ክሮሺያ ደግሞ ከፓናማ ጋር ትጫወታለች።

ይህ ትላንት ማታ በእንግሊዝ እና በክሮሺያ መካከል የተደረገው ጨዋታ ታክቲክ ብቻ ሳይሆን የልብ እና የነፍስ ፍልሚያ የነበረበት፣ መላውን የእግር ኳስ አፍቃሪ ያስደመመና ለረጅም ጊዜ ሲታወስ የሚኖር ታሪካዊ ጨዋታ ነበር።

እንደ Sky Sports ፣ BBC እና ESPN ያሉ የዓለም ታዋቂ የስፖርት ተንተኞች የእንግሊዝን ወጣት ተጫዋቾች ፍጥነት፣ የማጥቃት መስመር ድፍረት እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ያሳዩትን የአእምሮ ጥንካሬ አድንቀዋል።

በተለይም በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ እንግሊዝ ያደረገችው ፈጣን የታክቲክ ሽግግር እና የተጫዋቾች ቅያሪ ጨዋታውን ሙሉ በሙሉ የቀየረ ነበር ተብሏል።

ውጤቱ 2 ለ 2 በነበረበት ወሳኝ ቅፅበት የእንግሊዝ መስመር ተጫዋቾች በጥልቀት በመግባት ያስቆጠሯት 3ኛ ግብ የክሮሺያን ተከላካዮች ስነ ልቦና በመስበር ለ4 ለ 2 ውጤት ዋነኛ መንገድ ከፍታለች።

ክሮሺያም በበኩሏ በለመደችው መረጋጋትና በአስደናቂ የአማካይ መስመር ቁጥጥር በቀላሉ እጅ እንደማትሰጥ በድጋሚ አስመስክራለች።

በዓለም ዋንጫው ላይ እንደ ፈረንሳይ፣ ብራዚል እና አርጀንቲና ያሉ ፈታኝ ቡድኖች ቢኖሩም እንግሊዝ ትናንት ባሳየችው አይነት የታክቲክ ብስለትና ድንቅ ብቃት ከቀጠለች ግን የስልሳ ዓመታቱን ዋንጫ አልባ መንገድ በመቀየር ዘንድሮ ዋንጫውን ይዛ ወደ ሀገሯ የመመለስ ዕድሏ በጣም ሰፊ መሆኑን ተንተኞች ጠቁመዋል።

የ32 ዓመቱ ሃሪ ኬን በአጠቃላይ ለብሔራዊ ቡድኑ 81 ግቦችን በማስቆጠር የምን ጊዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ተጫዋች ሲሆን በቀጣይ ጨዋታዎች ግብ የሚያስቆጥር ከሆነ ከጋሪ ሊንከር በመብለጥ በዓለም ዋንጫ ውድድር የምን ጊዜም የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት ክብረ ወሰኑን በብቸኝነት የግሉ ያደርጋል።

አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን) 🇬🇧

#worldcup #englandfootball #ThreeLions #harrykane #goals #sports #ebcsport #EBC #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: