#Ethiopia | በሜክሲኮ ሲቲው ታሪካዊ የአዝቴካ ስታዲየም ወደ 80 ሺህ በሚጠጉ ተመልካቾች ፊት የተደረገው የኮሎምቢያ እና የኡዝቤኪስታን ጨዋታ የየምድቡን መጀመሪያ ዙር ፍልሚያዎች አጠናቋል።
በዚህ ጨዋታ ኮሎምቢያ ተጋጣሚዋን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ብትችልም የጨዋታው እንቅስቃሴ ግን የውጤት ሰሌዳው እንደሚያሳየው ማራኪ እና ሳቢ አልነበረም።
በ41ኛው ደቂቃ ላይ ጀፈርሰን ሌርማ ከረጅም ርቀት ያሻገረውን ኳስ ዳንኤል ሙኖዝ በግሩም የቮሊ ምት አስቆጥሮ ኮሎምቢያን ቀዳሚ አድርጓል።
ከዚህ ግብ በፊት ሉዊስ ዲያዝ የሞከራት ኳስ በግቡ ቋሚ የተመለሰችበት ሲሆን ኡዝቤኪስታን በመጀመሪያው አጋማሽ ምንም ዓይነት የግብ ሙከራ ሳታደርግ ወደ ዕረፍት አምርታለች።
ከዕረፍት መልስ በአሰልጣኝ ፋቢዮ ካናቫሮ የሚመራው የኡዝቤኪስታን ቡድን የተሻለ የማጥቃት እንቅስቃሴ ማሳየት የቻለ ሲሆን በ60ኛው ደቂቃ ላይ አቦስቤክ ፋይዙላቭ ከኤልዶር ሾሙሮዶቭ የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ ቡድኑን አቻ አድርጓል።
ይሁን እንጂ የኡዝቤኪስታን ደስታ ከአምስት ደቂቃዎች በላይ አልዘለቀም። በመሃል ሜዳ ላይ የተነጠቀውን ኳስ መነሻ በማድረግ ኮሎምቢያውያን የሰነዘሩትን ፈጣን የመልሶ ማጥቃት ሉዊስ ዲያዝ ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን ዳግም መሪ ማድረግ ችሏል።
ኡዝቤኪስታን ጨዋታውን አቻ ለማድረግ ብትሞክርም በጭማሪ ሰዓት 90 ከ 9ኛው ደቂቃ ላይ ሊያንድሮ ካምፓዝ በጭንቅላቱ ሶስተኛውን ግብ በማስቆጠር የኮሎምቢያን ባለሦስት ነጥብ ባለቤትነት አረጋግጧል።
#WorldCup #Colombia #Uzbekistan #Football #Azteca #LuisDiaz #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.