የ52 ዓመታት በኋላ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ጎል አገባች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የዓለም ዋንጫ ውድድር በከፍተኛ እልህ አስጨራሽ ጨዋታዎች የቀጠለ ሲሆን፥ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፖርቹጋል እና የዲሞክራቲክ ኮንጎ ፍልሚያ በአንድ አቻ ውጤት ተጠናቋል።

ይህ ጨዋታ በማዕድን ሀብቷ ለምትታወቀው አፍሪካዊቷ ሀገር ልዩ የታሪክ ምዕራፍ የተጻፈበት ሆኗል። ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ ማለትም ከ52 ዓመታት የጎል ድርቅ በኋላ በዓለም ዋንጫ ታሪኳ የመጀመሪያዋን ግብ ማሥቆጠር ችላለች።

በኒውካስትል ቆይታው አስቸጋሪ የውድድር ዘመን ያሳለፈውና ዘንድሮም ከጉዳት ጋር ሲታገል የነበረው ዮና ዊሳ ለሀገሩ ይህንን ወሳኝ እና ታሪካዊ ግብ አስገኝቷል።

ሀገሪቱ ቀደም ሲል በታዋቂው ፕሬዝዳንት ሞቡቱ ሴሴሴኮ ዘመን ዛየር በሚል ስያሜዋ በ1974ቱ የምዕራብ ጀርመን የዓለም ዋንጫ ላይ ተሳትፋ ነበር። በወቅቱ በምድብ ጨዋታዎች ከዩጎዝላቪያ፣ ስኮትላንድ እና ብራዚል ጋር ተጫውታ 14 ጎሎች ሲቆጠሩባት እሷ ግን አንድም ጎል ሳታስቆጥር በቶሎ መሰናበቷ ይታወሳል።

አሁን ግን ዊሳ ይህንን ታሪክ ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል።

በሌላ በኩል በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ፖርቹጋል በጁኣ ኔቬስ አማካኝነት መሪነቱን ይዛ የነበረ ቢሆንም ማቆየት አልቻለችም።

በዚህ ጨዋታ ላይ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ በ5 የዓለም ዋንጫዎች ላይ በመሳተፍ ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ያለውን ታሪካዊ ክብረወሰን ለመጋራት በቅቷል።

#WorldCup #Football #DRCongo #Portugal #YoaneWissa #Ronaldo #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2