የታመመች ዶሮውን ለማሳከም ወደ ሰው ሆስፒታል የገሰገሰው የ12 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ​በአማራ ክልል ደንበጫ ከተማ የሚኖረው የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የታመመች ዶሮውን ለማሳከም ወደ ሰው ሆስፒታል የገሰገሰው የ12 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ታዳጊ
​በአማራ ክልል ደንበጫ ከተማ የሚኖረው የ12 ዓመቱ ማርቆስ አባየ፥ ውድ ዶሮው በመታመሟ ምክንያት ወደ ደንበጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በመውሰድ የብዙሃኑን ልብ ማርኳል።
ታዳጊው ሆስፒታሉ ለሰዎች ብቻ መሆኑን ባለማወቅ ዶሮዋን አቅፎ ከነርሶች ጋር ሲነጋገር የሚያሳየው ቪዲዮ በቲክቶክ ላይ ከ700 ሺህ በላይ እይታን አግኝቷል።
​በወቅቱ በሆስፒታሉ የነበረው ነርስ ኡመር ጫኔ ታዳጊውን ወደ እንስሳት ሕክምና ቢመራውም፥ የማርቆስ ርኅራኄ ግን የአገር ውስጥና የውጭ ሚዲያዎችን ትኩረት ስቧል።
ማርቆስ በክልሉ በነበረው ግጭት ምክንያት ካያቶቹ ተለይቶ ወደ አጎቱ ሲመጣ ዶሮዋ በስጦታ የተሰጠችው ነበረች። ይህን የልጁን መልካምነት የተመለከተ አንድ የአገር ውስጥ የዶሮ እርባታ ኩባንያ ለታዳጊው 100 ዶሮዎችንና የእርባታ ስልጠና እንደሚለግስ አስታውቋል።
ቢቢሲ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1