ሜሎኒ ‹‹ፎቶ እንነሳ ብላ ለመነችኝ›› በሚል ትራምፕ የሰጡት አስተያየት በጣሊያን የፖለቲካ ተቃውሞ ቀሰቀሰ

- Advertisement -
Sidebar AD

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር የአሜሪካው ፕሬዝዳንት አባባል ‹‹ፈጽሞ ከእውነት የራቀ›› ነው ሲሉ አዲሱ ግጭት በአሜሪካ እና በአውሮፓ ህብረት አጋሮች መካከል ያለውን ውጥረት አመላክቷል።

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፤ በቅርቡ በተካሄደው የቡድን 7 ጉባኤ ላይ ፎቶ ለመነሳት ‹‹ለምናኛለች›› በሚል ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ላቀረቡት ክስ ጠንከር ያለ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ይህ አባባል በጣሊያን ከፍተኛ የፖለቲካ ተቃውሞ አስነስቷል።

‹‹አንዳንድ ነገሮች አፋጣኝ ምላሽ ይገባቸዋል። የዶናልድ ትራምፕ ንግግሮች ሙሉ በሙሉ ፈጠራ ናቸው፡፡እውነቱን ለመናገር በነገሩ ግራ ተጋብቻለሁ›› ሲሉ ሜሎኒ በማህበራዊ ሚዲያ በለቀቁት ቪዲዮ ተናግረዋል።

‹‹የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከአጋሮቹ ጋር ለምን እንዲህ አይነት ባህሪ እንደሚያሳይ አላውቅም፤ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ምዕራባውያንን እና አሜሪካን በሚቃወሙ ጠላቶች ላይ የማያሳየውን ቁርጠኝነት በአጋሮቹ ላይ ማሳየቱ ያሳዝናል ከማለት ውጪ ሌላ የምለው የለም›› ሲሉ አክለዋል።

‹‹ነገር ግን አንድ ሊያስታውሰው የሚገባ ነገር አለ፤ እኔም ሆንኩኝ ጣሊያን መቼም አንለምንም።››

ላ7 ትራምፕ ‹‹ፎቶ እንድንነሳ ለመነችኝ። ከእኔ ጋር ፎቶ ለመነሳት በጣም ፈልጋ ነበር… ባልነሳም ደስ ይለኝ ነበር፣ ግን አሳዘነችኝ›› ማለታቸውን ዘግቧል።

ይፋ የሆነው ይህ ንግግር በጣሊያን ውስጥ ጠንካራ ተቃውሞ ያስከተለ ሲሆን፤ የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰርዘዋል።

ታጃኒ ኤክስ በተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ‹‹ትራምፕ በጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ላይ የተናገሩት ከባድ እና አስጸያፊ ቃላት መላውን ጣሊያንን የሚሳደቡ ናቸው። በዚህ ምክንያት ሰኔ 21 እና 22 ወደ አሜሪካ ለማድረግ አቅጄው የነበረውን ጉብኝት ለመሰረዝ ወስኛለሁ›› ሲሉ ጽፈዋል።

ይህ ክስተት ቀደም ሲል የቅርብ ግንኙነት በነበራቸው በጣሊያን እና በአሜሪካ መሪዎች መካከል እያደገ የመጣውን ውጥረት ያሳያል።

ሜሎኒ ባለፈው ዓመት በትራምፕ በዓለ ሲመት ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙ ብቸኛ የአውሮፓ መሪዎች አንዷ ነበሩ።

እስከዳር ግርማ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: