በሜሎኒና በትራምፕ መካከል የተቀሰቀሰው ፍጥጫ
#Ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በቡድን 7 ጉባኤ ወቅት የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ፎቶ ለመነሳት እንደለመኗቸውና አዝነውላቸው አብረዋቸው ፎቶ መነሳታቸውን ለጣሊያኑ ላ7 ቲቪ መናገራቸውን ተከትሎ.፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል።
በትራምፕ ንግግር ክፉኛ የተቆጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ሜሎኒ በቪዲዮ ባስተላለፉት ምላሽ፣ የትራምፕ ንግግር ሙሉ በሙሉ የፈጠራ ወሬ መሆኑን በመግለጽ.፣ “እኔና ጣሊያን ፎቶ ለመነሳት ማንንም አንለምንም” ሲሉ በቁጣ አጣጥለውታል።
ፕሬዝደንቱ በአጋር ሀገራት ላይ እንዲህ አይነት ድርጊት ሲፈጽሙ ይህ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነም ሜሎኒ አክለው ገልጸዋል።
ይህንን ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየሻከረ የመጣ ሲሆን፣ የጣሊያኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ታጃኒ ወደ አሜሪካ ሊያደርጉት የነበረውን ይፋዊ ጉዞ ወዲያውኑ ሰርዘዋል።
ሚኒስትሩ ከአሜሪካው አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ቀጠሮ የተሰረዘው በዚህ እያገረሸ በመጣው አለመግባባት ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።
#GiorgiaMeloni #DonaldTrump #Italy #USA #DiplomacyDrama #BreakingNews #G7 #WorldPolitics
Source: GetuTemesgen









No comments yet.