ተከሳሽ ዋአልኤ ዋርዳ የቅሚያ ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ አካባቢ ነው።
የግል ተበዳይ በግምት ከምሽቱ 1፡30 ሰዓት ገደማ ከስራ ወደ መኖሪያ ቤታቸው በሚጓዙበት ወቅት ተከሳሹ ከኃላቸው በመምጣት የግል ተበዳይ ይዘውት የነበረውን የእጅ ቦርሳ ቀምቶ ለማምለጥ ሲሞክር በፖሊስ አባላትና በአካባቢ ጥበቃዎች ትብብር እጅ ከፈንጅ መያዙን በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የካራ ቆሬ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ተከሳሹ በቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅትም በቦርሳው ውስጥ የነበረውን ስማርት ሞባይልና 8 ሺህ 550 ብር በአጠቃላይ 23 ሺህ 700 ብር የሚገመት ንብረት በማስመለስ አስፈላጊው ምርመራ ከተጣራበት በኃላ አቃቤ ህግ ክስ እንደመሰረተበት ፖሊስ ገልጿል።
የተከሳሽ ዋአልኤ ዋርዳን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ፈጣን የወንጀል ችሎት ጥፋተኝነቱን በሰው ማስረጃ ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሹን ያስተምራል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት በፈፀመው የቅሚያ ወንጀል በ2 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበታል።
ማንም ሰው ወንጀል ፈፅሞ ከህግ እንደማያመልጥና የህግ የበላይነት እንደሚረጋገጥ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህብረተሰቡ ወንጀል እንዳይፈፀምበት ተገቢውን ጥንቃቄ በማድረግ እንደ ከዚህ ቀደሙ ለፀጥታ አካላት እየሰጠ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል።
Addis Ababa police
Source: Yeneta Tube








No comments yet.