የእናቱን አስክሬን ቤት አስቀምጦ የእናቱን ቃል ለማክበር የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና ከቀብር በፊት እና በኃላ ለፈተና የተቀመጠው ካሊድ
#Ethiopia | ይሕ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታዳጊ ካሊድ ይባላል ገና የአስራ አራት ዓመት ልጅ ነው።ከሑለት ታናናሽ ወንድሞቹ ጋር በሸገር ከተማ አስተዳደር ኤካ ጣፎ ክፍለ ከተማ ከእናቱ ጋር ይኖራል።
ካሊድ ከእናቱ ጋር ሲኖር ወላጅ አባቱ ከእነርሱ ርቆ ሌላ ትዳር መስርቶ ጅጅጋ ከተማ ይኖራል። ካሊድ ሠሞኑን እናቱ ታምወው በነበረበት ወቅት እኔ አንድ ነገር ብሆን ምንም ቢፈጠር አመት የለፋሕበትን ፈተና እንዳታቋርጥ ብለው ቃል ያስገቡታል።
እናትም በነጋታው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ሊሲጥ ሠዓታት ሲቀረው ሕይወታቸው ያልፋል።ካሊድ በእናቱ ሞት ከፍተኛ ሐዘን ቢሰማውም ለእናቱ የገባው ቃል አክብሮ የእናቱን አስክሬን እቤት ጥሎ የጥዋት ፈተናውን ተፈተነ።
ካሊድ ከሠዓት እናቱን አልቅሶ ቀብሮ ተመልሶ የከሰዓት ፈተናውን ተፈተነ።የዚሕ የአስራ አራት አመት ታዳጊ የሕይወት ፈተና ብዙዎችን በሐዘን ማስለቀሱን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።
credit : ዳጉ ጆርናል
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.