ታክስ ከፋዮች ከደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ የ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ታክስ ከፋዮች ከደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ እንዲኖራቸው የሚያስገድድ መመርያ ወጣ
የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ሕጉ መሠረት የሒሳብ መዝገብ የሚይዙ ታክስ ከፋዮች፣ ራሱ ካበለፀገው የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት እንዲጠቀሙ የሚያዝ መመርያ ተግባራዊ አደረገ።
ገቢዎች ሚኒስቴር የራሳቸውን የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አበልፅገው ወይም ከአልሚዎች ገዝተው በማስፈቀድ ለሚጠቀሙ ታክስ ከፋዮች ዕውቅና እንዲያገኙ፣ የክትትልና ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋትና አሠራራቸውን በሕግ ለመወሰን የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ አስተዳደር ሥርዓት መመርያ ቁጥር 1142/2018ን ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ተገልጿል፡፡
የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ስለመጠቀም በሚደነግገው የመመርያው አንቀጽ 19፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ካዘጋጀው የኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት፣ የሒሳብ መዝገብ በሚይዙ ሁሉም ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይደነግጋል፡፡
የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት፣ ታክስ ከፋዮች ሽያጫቸውን ለመመዝገብና የሽያጭ መረጃዎችን በቀጥታ በኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ሥርዓት ለማስተላለፍና ለመመዝገብ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡
ማንኛውም ታክስ ከፋይ በፈቃደኝነት ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት መጠቀም እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡
ሆኖም በርካታ ደረሰኞችን የሚያመነጩና አሠራራቸው ለኦዲትና ለክትትል አመቺ የሆኑ ባንኮች፣ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያዎች፣ የዲጂታል ከፍያ አሳላጮች፣ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ለሸማች ወይም ለግል አገልግሎት በሚውሉ ግብይቶችና አገልግሎቶች ላይ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር በቀጥታ መገናኘት ሳያስፈልጋቸው፣ ደረሰኝ የሚሰጡበትን አሠራር ሚኒስቴሩ በልዩ ሁኔታ ሊፈቅድ ይችላል ተብሏል፡፡
አጠቃላይ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ፈቃድ አሰጣጥ ሁኔታን በሚመለከት በተደነገገው የመመርያው ከፍል፣ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሶፍትዌር ደኅንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ሊያቀርብ እንደሚገባ ተደንግጓል፡፡
በተጨማሪም በኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓቱ ውስጥ የተተገበሩ የማንነት ማረጋገጫ፣ የግንኙነት መመስጠሪያና ሌሎች የደኅንነት አሠራሮችን መተግበሩና በዲጂታል ፊርማ የተረጋገጠ ግንኙነትና የመረጃ መላላክን ማስቻሉ ሊረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከቷል፡፡
#ሪፖርተር
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2