የሕወሓት ቡድን ለአሜሪካ መልስ ሰጠ!
የአሜሪካ መንግሥት በፓርቲው አመራሮች ላይ የጣለው የቪዛ ገደብ ያልተሟላ እና ሚዛናዊነት የጎደለው ግምገማ ላይ የተመሠረተ ነው ሲል የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ክፉኛ ኮነነ።
ሕወሓት ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት የአሜሪካን ሚና እንደሚያከብር ቢገልጽም፤ አዲሱ የማዕቀብ ውሳኔ ግን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ያሉበትን ግዴታዎች በተደጋጋሚ አለመወጣቱን ወደ ጎን በመተው፣ ኃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ በሕወሓት ላይ ብቻ የሚጭን በመሆኑ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል።
የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ከሦስት ዓመታት በላይ ቢያልፉም፣ የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት መመለስ፣ የተፈናቃዮች መዋቅራዊ ዕርዳታ፣ የውጭ (የፌደራል ያልሆኑ) ኃይሎች ከትግራይ መሬት መውጣት እና የህወሓት ሕጋዊና ፖለቲካዊ ሰውነት ዕውቅና ማግኘት የተባሉት ቁልፍ ድንጋጌዎች አሁንም አልተተገበሩም ብሏል።
@Seledadotio

No comments yet.