#Ethiopia | በሰሜን ካሮላይና ኒውተን ከተማ በሚገኝ የቤት ዕቃዎች ማምረቻ ድርጅት ውስጥ የ85 ዓመቱ ዊላርድ ብላክ የ59 ዓመቱን የቢዝነስ አጋራቸውን ሮበርት አርጉኤለስን በጥይት መትተው መግደላቸውን ፖሊስ አስታውቋል። ግድያው የተፈጸመው ፍርድ ቤት አዛውንቱ ለአጋራቸው ከ300 ሺህ ዶላር በላይ እንዲከፍሉ በወሰነባቸው በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ነው።
እንደ መርማሪዎች ገለጻ ሁለቱ ግለሰቦች በድርጅቱ የአክሲዮን ድርሻና በገንዘብ ክፍያ ዙሪያ በሕግ ሲከራከሩ የቆዩ ሲሆን በዕለቱ አዛውንቱ ያቀረቡት የስምምነት ማሻሻያ ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ነበር። በጥይት የተመቱት አርጉኤለስ በፈጣን ሕክምና ዕርዳታ ሳይተርፉ እዛው የሞቱ ሲሆን ተጠርጣሪው ብላክ በቁጥጥር ሥር ውለው ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ሟቹ አርጉኤለስ የቢዝነስ ሰው ከመሆናቸውም በላይ በአካባቢው ትምህርት ቤት ቦርድ አባል በመሆን ማኅበረሰባቸውን በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩ መሆናቸውን የወረዳው የትምህርት ባለሥልጣናት ገልጸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.