ሕወሓት የአሜሪካ መንግስት በአባላቱ ላይ የጣለውን የቪዛ ገደብ «ያልተመጣጠነ እና ወገንተኛ» ሲል አወገዘ
ህወሓት ውሳኔው በክልሉ ላለው አለመረጋጋት ተጠያቂነቱን በሙሉ በትግራይ አመራር ላይ ብቻ የጫነ “ያልተሟላ ግምገማ” ነው ብሏል።
ይህ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ የተነሳው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢሚግሬሽን እና ዜግነት ህግ አንቀጽ 212(አ)(3)(ሲ) መሰረት የቪዛ ገደቦችን ይፋ ካደረገ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ቶማስ ቶሚ ፒጎት እንደገለጹት፥ እገዳው ያነጣጠረው የሰላም ሂደቱን እያደናቀፉ ነው የተባሉትን የሕወሃት “ፅንፈኛ አባላት” እና የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን ነው። ይህም በትግራይ ኃይሎች እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት መካከል በቅርቡ ከተከሰቱት ቀጥተኛ ግጭቶች በኋላ የመጣ እርምጃ ነው።
@Seledadotio

No comments yet.