መረጃዓለም ባንክ፣ ለጅቡቲ-ኢትዮጵያ የመንገድ ኮሪደርን ለማሻሻል ተጨማሪ 45 ሚሊዮን ዶላር ፈቀደ። የአሁኑ ተጨማሪ የገንዘብ ድ…

- Advertisement -
Sidebar AD
መረጃ‼️
ዓለም ባንክ፣ ለጅቡቲ-ኢትዮጵያ የመንገድ ኮሪደርን ለማሻሻል ተጨማሪ 45 ሚሊዮን ዶላር ፈቀደ።
የአሁኑ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ፣ ባንኩ ለመንገድ ልማቱ እስካሁን የሠጠውን ገንዘብ 205 ሚሊዮን ዶላር ያደርሠዋል።
ባንኩ የገንዘብ ድጋፉ ቀጠናዊ ትስስርን ለማጠናከር፣ የሎጅስቲክ አቅምን ለማሳደግና የመንገድ ደኅንነትን ለማሻሻል እንደሚውል ገልጧል። 
መንገዱ ከፍተኛ ሙቀትንና ዝናብን እንዲቋቋም ኾኖ እንደሚሻሻልም ባንኩ ጠቅሷል።
የመንገድ ኮሪደሩ ተሽከርካሪዎች ለጉዞ እና የድንበር ኬላ ለማለፍ የሚፈጅባቸውን ጊዜ ይቀንሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የትራፊክ አደጋዎችንም በ30 በመቶ ሊቀንስ ይችላል ተብሎለታል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: