#Ethiopia | የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰነዘሩባቸው ተደጋጋሚ ትችቶች ላይ ጠንካራ ምላሽ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የሳቸው ተወዳጅነት በትራምፕ ወዳጅነት ላይ እንደማይመሰረትና ዋና ግባቸው የኢጣሊያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር እንደሆነ ገልጸዋል።
በሀገሪቱ ውስጥ ስለሚገኙት የአሜሪካ ወታደራዊ ካምፖች አጠቃቀም ሲያብራሩም ኢጣሊያ ሉዓላዊት ሀገር መሆኗንና ስምምነቶቹ እስከ አሁን እንደተከበሩ ሁሉ ወደፊትም እንደማይጣሱ አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ጠቅላይ ሚኒስትሯ፣ “የእኔ ተወዳጅነት የእርስዎ ጉዳይ አይደለም ይልቁኑ እርስዎ በእርስዎ ተወዳጅነት ላይ ቢያተኩሩ ይመረጣል” ሲሉ ለትራምፕ ቀጥተኛ ምክራቸውን ለግሰዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.