ከገብርኤል ለገብርኤል

- Advertisement -
Sidebar AD

ታላቁ የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል ዓመቱን ሙሉ ሕዝበ ክርስቲያን የማይለየው በተለይም የታህሣስ እና ሐምሌ ዓመታዊ በዓላት ደግሞ እጅግ በርካታ ምዕመን የሚጎርፍበት ስዕለቱ የሞላለትና እንዲሁ ለተራዳኢነቱ ፍቅሩን ለመግለጥ በሚመጣ ህዝብ የሚጥለቀለቅበት ገዳም ነው ።

እንደየአቅማችንም የምንለግሰው ስዕለት አስራት በኩራት ምፅዋትና ሌሎች ስጦታዎቻችን በሙሉ ከ50 ዓመታት በፊት ጀምሮ ወደ ጠቅላይ ቤተክህነት እንዲተላለፍ ተወስኖ በሚገኘው ጠቅላላ ገቢ በሁሉም አህጉረ ስብኩት ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት፣ የአብነት ት/ቤቶች፣መንፈሳዊ ኮሌጆች፣ቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ፣አባ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ኮሌጅ፣ሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ እና ለሌሎችም የትምህርት ተቋማት መመስረትና ለበርካታ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና ቋሚ መሰረተ ልማቶች እንዲውል በመደረጉ ለሁለንተናዊ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ችግር ፈቺ፣ የልማት ተሳታፊ፣ ድርና ማግ ፣ ምሰሶና ማገር ለመሆን በቅቷል።

በእነኚህ ረጅም ዓመታት ለቁልቢ በሰጣችሁት ስጦታ በየአቅራቢያሁ ያሉ የቤተክርስቲያን መሰረተ ልማቶች ሁሉ የቁልቢ ገብርኤል አሻራ ታትሞባቸዋል ።

በእድሳት ላይ የሚገኘው ቁልቢ ገብርኤል በቅርቡ በተለመደው ቤተክርስትያንን የማቅናት ተግባሩ የመቃጠል አደጋ የደረሰበት የአርሲ ጠለታ ገብርኤልን ለማስገንባት በዝግጅት ላይ ይገኛል ።

የቁልቢ ውለታ ያለባችሁ ተቋማት፣ ስዕለታችሁ የተሰማ ፣ በተስፋ የምትጠብቁ ምዕመናን ኑ የዕንባ አባሹ ቁልቢ ገብርኤልን እናድስ የአርሲን ጠለታ እንገንባ ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ ።

ድጋፍ ለማድረግ፡-

– CBE ንግድ ባንክ 1000759706165
– ⁠Awash አዋሽ ባንክ 013521749645300
– ⁠Abyssinia አቢሲኒያ ባንክ 2556 02373
– ⁠Dashen ዳሸን ባንክ 517116 3880011
– ⁠Hibret ሕብረት ባንክ 109071323 4152990
– ⁠COOP ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ 1063900050599
– ⁠Ahadu አሐዱ ባንክ 0093543501901
– ⁠Abay አባይ ባንክ 18411129 58315015
– ⁠Anbesa አንበሳ ባንክ 00313350582
– ⁠Amhara አማራ ባንክ 99000 50109805

Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1