‎ለ60 ዓመታት የታማኝነት ጉዞ በጋራ እንሩጥ!” በሚል መሪ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​ለስድስት አስርት ዓመታት በአገልግሎት የዘለቀው እና ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኘው ኮሜርሻል ኖሚኒስ፣ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በተለያዩ ኩነቶች በድምቀት እያከበረ ይገኛል።

‎”ለ60 ዓመታት የታማኝነት ጉዞ በጋራ እንሩጥ!” በሚል መሪ ቃል፣ ዛሬ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ተደርጓል።

‎በዚህ መርሐግብር ላይ የሥራ አካባቢን ጤንነት ከመጠበቅ ባለፈ፣ “ስፖርት ለሁሉም” የሚለውን ሀገራዊ መሪ ቃል በማጉላት ህብረተሰቡን በአንድነት የሚያገናኝ ልዩ መድረክ መሆኑን በመርሐግብሩ ላይ ተገልጿል።

‎የኮሜርሻል ኖሚኒስ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮማንደር ጥላቸው ፀጋዬ እንደገለጹት፣ ይህ የ60 ዓመት ጉዞ የጋራ ጥረት ውጤት የሆነ የቅብብሎሽ ሂደት ነው። ተቋሙ ካለፉት ስድስት አስርት ዓመታት ልምድ በመቅሰም፣ ለወደፊት ግዙፍ እና ዘመናዊ የልማት ስራዎች ዝግጅቱን አጠናቋል።

‎​አሁን ላይ በሀገሪቱ 30 ቅርንጫፎች እና ከ40 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ኮሜርሻል ኖሚኒስ፣ በአብዛኛው ወጣቶች እና ሴቶች በስራው አለም ተሳታፊ የሚሆኑበት ሰፊ መድረክ ፈጥሯል።

‎ኩባንያው በሚቀጥሉት ዓመታት በ ጋርመንት ፋብሪካ ግንባታ፣ በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር፣ እንዲሁም በሪል ስቴት ልማት ዘርፎች በመሰማራት አቅሙን ለማሳደግ እቅድ ይዟል።

‎በተለይም በዘመናዊ የጽዳት ማሽኖች እና በሌሎች መሰረተ ልማቶች ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት እና የስራ እድል በመፍጠር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል።

ኮማንደር ጥላቸው እንደተናገሩት፣ ኩባንያው ከቀላል የንግድ ተቋምነት ተሻግሮ፣ በርካታ ቅርንጫፎችን የያዘ ግዙፍ የኮሜርሻል ኖሚኒስ ግሩፕ ለመሆን እና ከሀገር አልፎ በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን እየሰራ ይገኛል።

‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ







Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2