በዛሬው ዕለት፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ የእግዚአብሔር ሰው ነቢይ ኢዩ ጩፋ የማስተርስ ኦፍ ክርስቲያን ቲዎሎጂ (Maste

- Advertisement -
Sidebar AD

በዛሬው ዕለት፣ ሰኔ 14 ቀን 2018 ዓ.ም.፣ የእግዚአብሔር ሰው ነቢይ ኢዩ ጩፋ የማስተርስ ኦፍ ክርስቲያን ቲዎሎጂ (Master of Christian Theology) ዲግሪ ምረቃ ሥነ-ሥርዓታቸው በበርካታ እንግዶች፣ ቅዱሳን፣ ወዳጆችና አገልጋዮች በተገኙበት እጅግ ደማቅና የተዋበ ሁኔታ ተካሂዷል።

ነቢይ ኢዩ ጩፋ ላለፉት ዓመታት ትምህርታቸውን በትጋት፣ በጽናትና በታማኝነት ሲከታተሉ ቆይተዋል። ሆኖም ግን፣ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወራት በፊት በእናታቸው ወደ ጌታ ማረፍ ምክንያት በጥልቅ ሐዘን ውስጥ ስለነበሩ፣ የምረቃ ሥነ-ሥርዓታቸውን በታቀደለት ጊዜ ማካሄድ አልቻሉም። ሐዘንና ደስታ በአንድ ጊዜ አብረው ሊከበሩ እንደማይችሉ በመግለጽ፣ ለትምህርት ተቋሙ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ፈቃድ ተሰጥቷቸው የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ለዛሬው ዕለት ተላልፎ ተካሂዷል።

በሌላ በኩል፣ ነቢዩ የዶክትሬት (PhD) ትምህርታቸውን ያለማቋረጥ በመቀጠላቸው፣ በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እንደሚያገኙም ተረጋግጧል።

እንደ መምህራኖቻቸው ገለጻ፣ ነቢይ ኢዩ ጩፋ በትምህርታቸው ጠንካራ፣ ትጉህና ተስፋ ሰጪ ተማሪ የነበሩ ሲሆን፣ በጥናት ዘርፍም የተለየ ብቃት አሳይተዋል። በምረቃ መድረኩ ላይ ያቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍም ለተሰብሳቢው ማኅበረሰብ ይፋ ተደርጓል።

በተያያዘም፣ ነቢይ ኢዩ ጩፋ የስኬታቸው ምንጭ ለሆነው ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ካቀረቡ በኋላ፣ ለክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን፣ ለቦርድ አባላት፣ ለጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች፣ ለአብሮ ሠራተኞቻቸው (ፓርትነሮች)፣ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ለሚገኙ ወዳጆቻቸው፣ እንዲሁም ለኮሌጁ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች ከልብ የመነጨ ታላቅ ምስጋና አቅርበዋል።

በአጠቃላይ፣ የእግዚአብሔር ሰው ነቢይ ኢዩ ጩፋ የማስተርስ ዲግሪ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት በበርካታ ቅዱሳን፣ ወዳጆችና እንግዶች በተገኙበት እጅግ ደማቅና ታሪካዊ በሆነ ሁኔታ ተካሂዶ ተጠናቋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: