♦️
♦️አዲሱ አህጉራዊ ኃላፊነትም ኢትዮጵያ በአፍሪካ የፖለቲካ፣ የስፖርት እና የተቋማዊ አመራር ዘርፎች ያላትን ተሰሚነት የበለጠ ያጠናክራል ተባለ
#Ethiopia | የፓን-አፍሪካ ፓርላማ ፕሬዚዳንት ፋቴህ ቡትቢግ ለኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በላኩት የእንኳን ደስ አላችሁ ደብዳቤ፣ ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጋዮ የፓን-አፍሪካ ፓርላማ 1ኛ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው ለኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ እንዲሁም ለዶ/ር አሸብር እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በደብዳቤያቸው ዶ/ር አሸብር በአህጉራዊ ደረጃ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ የኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፉን እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ጋዮ በፓን-አፍሪካ ፓርላማ ያላቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት በመሆን ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያደርጉ ቆይተዋል።
በተለይም የኦሎምፒክ እንቅስቃሴን በማጠናከር፣ ለወጣት አትሌቶች ዕድል በመፍጠር እና የስፖርት ተቋማትን በማጎልበት ጉልህ ሚና ተጫውተዋል።
በአፍሪካ ደረጃም የስፖርት ትብብርን፣ የኦሎምፒክ እሴቶችን እና የወጣቶች ተሳትፎን ለማሳደግ የሚያደርጉት አስተዋፅኦ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።
ይህ አዲስ አህጉራዊ ኃላፊነትም ኢትዮጵያ በአፍሪካ የፖለቲካ፣ የስፖርት እና የተቋማዊ አመራር ዘርፎች ያላትን ተሰሚነት የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል።
የፓን-አፍሪካ ፓርላማ በደብዳቤው ዶ/ር አሸብር የ1ኛ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ተግባራቸውን በውጤታማነት እንዲያከናውኑ የሚያስፈልጉ ድጋፎች እንዲደረጉላቸው ጥሪ አቅርቧል።
N.B የፕሬዝዳንቱ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት(ደብዳቤ)ከዚህ ዘገባ ጋር አያይዘነዋል
✍️✍️በጋዜጠኛጨይስሀቅ በላይ (ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)

Source: GetuTemesgen









No comments yet.