ውለታ የማትረሳው ደቡብ ኮርያ

- Advertisement -
Sidebar AD

📌በኮርያ መንግስት ድጋፍ የተቋቋመው የኮርያ ዘማች የልጅ ልጆች ”ቃኘው ኳየር” የሙዚቃ ቡድን ዛሬ አመሻሸ ወደ ደቡብ ኮሪያ ይጓዛል

#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ወዳጅነት እና ባህል ይበልጥ ለማስተዋወቅ የተቋቋመው የቃኘው ኳየር የኅብረ ዝማሬ ቡድን ወደ ደቡብ ኮሪያ ሊጓዝ መሆኑ ተገለጸ።

በትናንትናው ዕለት ለሚዲያ ባለሙያዎች ቅድመ ትዕይንት የግምገማ ስራቸውን ያቀረቡት አባላቱ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ 35 የኮሪያ ዘማች የልጅ ልጆች ሲሆኑ ቡድኑ በኮሪያ የ38 ቀናት ቆይታ ይኖረዋል ተብሏል።

የጉዞው ዋና ዓላማ በደቡብ ኮሪያ በሚካሄደው 76ኛው የኮሪያ ዘማቾች በዓል ላይ ተገኝቶ የሁለቱን ሀገራት ባህል የሚያንጸባርቁ ዝግጅቶችን ማቅረብ ነው። ከልጆቹ በተጨማሪ አምስት ኢትዮጵያውያን እና ኮሪያውያን አስተባባሪዎች አብረው ይጓዛሉ ተብሏል።

ይህን ታሪካዊ ጉዞ እውን ለማድረግ ታዳጊዎቹ
በኮሪያ ጦርነት አርበኞች ድጋፍ ማኅበር በኩል
ከኢትዮጵያውያን እና ኮሪያውያን የሙዚቃና የዳንስ አሰልጣኞች ጋር በመሆን ከሶስት እስከ አራት ወራት ለሚደርስ ጊዜ ጠንካራ ልምምድ ሲያደርጉ ቆይተዋል።

በቆይታቸውም በአማርኛ እና በኮሪያኛ ቋንቋዎች ዝማሬዎችን የሚያቀርቡ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የትግርኛ፣ የኦሮምኛ፣ የአማርኛ እና ሌሎች የሀገራችንን ባህላዊ የሙዚቃ ትዕይንቶች በአንድ ላይ በማካተት የኢትዮጵያን ባህል ለኮሪያውያን ያስተዋውቃሉ።

ልጆቹ የኮሪያን ባህልና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን በኬ-ቢ-ኤስ እና በሌሎች አማራጮች በሚገባ የሚከታተሉ በመሆናቸው ለሀገሪቱ የተለየ ፍቅር እንዳላቸው እና ቋንቋውንም ከትምህርት ሰዓታቸው ውጭ በየሳምንቱ እሁድ እየተማሩ እንደሚገኙ የፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ገልጸዋል።

​የሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ትስስር “በደም የተሳሰረ” መሆኑን የሚያነሱት የዘማች ቤተሰቦች አቶ ኤፍሬም ሃ/ማርያም እና ወ/ሮ እናኑ አማረ በጦርነቱ ወቅት የቆሰለን ኮሪያዊ ለማትረፍ ሲሞክር አብሮት የተሰዋውን ኢትዮጵያዊ ወታደር ታሪክ እንደ ማሳያ ያነሳሉ።

የሁለቱ ጀግኖች አፅም በአዲስ አበባ በሚገኘው ሥላሴ ቤተክርስቲያን እና በኮሪያ ማረፉ ወዳጅነቱ የመሠረተውን ጥልቅ ትስስር ያሳያል።

በዚህም የተነሳ ኮሪያውያን ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ጊዜ ሐውልቱን ከመጎብኘት ባለፈ ለእነዚህ አባቶች ጸሎት አድርገው፣ አክብሮታቸውን ገልጸው እና እጅ ነስተው ነው የሚመለሱት።

በአሁኑ ወቅትም የኮሪያ መንግሥት የሚደግፈው የኮርያ ዘማቾች ድጋፍ ማህበር በመቋቋሙ በሕይወት ላሉ የኮሪያ ዘማቾች፣ ለቤተሰቦቻቸዎ እንዲሁም ለልጅ ልጆቻቸው የትምህርት እና ልዩ ልዩ የገንዘብ ድጋፎችን በማድረግ ውለታቸውን እየመለሱ ይገኛሉ።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1