#Ethiopia | የቱርክ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን እና የቤሺክታሽ ክለብ ታማኝ ደጋፊ የሆነው ኡዲ ኔኮ ባለው ለየት ያለና አስደናቂ የስታዲየም አቀራረብ በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሰፊ ትኩረት ስቧል።
ትክክለኛ ስሙ ኔጅደት ኦልቸርማን የሚባለው ይህ ታዋቂ ‘ሱፐር ፋን’ ሙሉ በሙሉ በጥቁር ቀለም የተቀባ ፊቱ፣ ደምቆ በሚታይ ነጭ ጸጉርና ጺሙ እንዲሁም በዓይኖቹ ዙሪያ በሳላቸው ነጫጭ ክብ ቅርጾች አማካኝነት በዓለም ዙሪያ ባሉ የስፖርት አፍቃሪያን ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ለመሆን በቅቷል።
ኡዲ ኔኮ ለሀገሩና ለሚወደው ክለብ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ለመግለጽ የሚጠቀምበት ልዩ የስዕል ጥበብና ገጽታ፣ ስታዲየም በተገኘ ቁጥር የብዙዎችን ቀልብ በቀላሉ እንዲስብ አድርጎታል።
ለአፍታም በማይቀዘቅዘው ስሜቱና በዚህ ለየት ባለ ማራኪ ገጽታው አማካኝነት ኡዲ ኔኮ በአሁኑ ወቅት የዓለም እግር ኳስ ደጋፊዎች በጉጉት ከሚጠብቃቸውና የስታዲየም ድምቀት ከሆኑት ድንቅ ደጋፊዎች መካከል ግንባር ቀደሙ መሆን ችሏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.