#Ethiopia | ዩክሬን በሩሲያ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ላይ ጥቃት መፈጸሟን ተከትሎ ጥቁር ጋዝ የቀላለቀ ዝናብ እየጣለ እንደሆነ ነዋሪዎች ገለጹ።
ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ ዩክሬን በሞስኮ ላይ ካደረሰቻቸው ጥቃቶች የከፋው ሲሆን፤ ዩክሬን ወደ ሩሲያ መዲና ወደ 200 የሚጠጉ ድሮኖችን ተኩሳለች።
የሞስኮ ሰማይ በጥቁር ጭስ እንደታፈነ እና 17 ሰዎች እንደተጎዱ አገረ ገዢው አንድሪ ቮሮብዮቭ ተናግረዋል።
በደቡብ ምሥራቅ ሞስኮ የሚገኙ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደገለጹት ዝናቡ ልብሳቸው ላይ “አስቀያሚ” ጥቁር ምልክት ይጥላል።
የሞስኮ ባለሥልጣናት “ጋዝ የቀላቀለ ዝናብ” መውረዱን ቢያስተባብሉም፤ በቴሌግራም ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ነዋሪዎች መስኮታቸውን እንዲዘጉ እና አስም ያለባቸው ሕጻናት እና አረጋውያን አካባቢው ለቅቀው እንዲወጡ አሳስበዋል።
የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት ወደ 1,000 የሚጠጉ የዩክሬን ድሮኖችን ማምከን ተችሏል።
በሞስኮ ደቡባዊ ግዛት በምትገኘው ሮስቶቭ የነዳጅ ፋብሪካ ላይ በደረሰው ጥቃት አንድ ሰው ተገድሏል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ እንዳሉት የድሮን ጥቃቱ ባለፈው ሳምንት ሩሲያ በቪቭ ላደረሰችው ድብደባ የአጸፋ ምላሽ ነው።
#BBC #Russia #Ukraine
#ጌጡተመስገን #ሚዲያኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen #Mediacommunication
Source: GetuTemesgen









No comments yet.