አርቲስት ካሙዙ ካሳ ምርጫውን ማሸነፉን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በየካ ክፍለ ከተማ በብልፅግና ፓርቲ ለምርጫ ቀርቦ የነበረው አርቲስት ካሙዙ ካሳ፣ በአካባቢው ነዋሪዎች ከፍተኛ ድምፅ ተሰጥቶት ማሸነፉን ይፋ አድርጓል። አርቲስቱ የምርጫ ውጤቱን ተከትሎ ለመራጮች ምስጋናውን አቅርቧል።

​ታዋቂው አርቲስት ካሙዙ ካሳ፣ በየካ ክፍለ ከተማ በተካሄደው ምርጫ ብልፅግና ፓርቲን ወክሎ በመወዳደር፣ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ማሸነፉን በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

​አርቲስቱ ባስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፣ ለምርጫው መሳካት ላደረጉት ድጋፍ የአካባቢውን ነዋሪዎች እና መራጮቹን አመስግኗል። “እንደ ብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ድምፅ በማግኘታችን እና በአካባቢው ማሸነፋችን ታላቅ ድል ነው” ሲል የገለጸው አርቲስት ካሙዙ፣ በድል አድራጊነት ስሜት ኢትዮጵያ አሸንፋለች የሚል መልዕክት አስተላልፏል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: