#Ethiopia | የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሌበር ፓርቲ መሪ ኬር ስታርመር ከሥልጣናቸው መልቀቃቸውን ይፋ አደረጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቁጥር 10 ዳውኒንግ ስትሪት ከሚገኘው ቢሯቸው ውጪ በሰጡት መግለጫ፣ ፓርቲያቸው መጪውን አጠቃላይ ምርጫ ለመምራት ብቁ መሆን አለመሆናቸውን ሲጠይቅ እንደነበረና እርሳቸውም ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ማግኘታቸውን በግልጽ ተናግረዋል።
በሥልጣን ዘመናቸው የወሰኗቸው ውሳኔዎች በሙሉ የሚወዷትን አገራቸውን ሁልጊዜም እንደሚያስቀድሙ የገለጹት ስታርመር በንግግራቸው ወቅት ስሜታዊ በመሆን ውድ ባለቤታቸውን ቪክን “ጠንካራ” በማለት አመስግነዋል እንዲሁም ለልጆቻቸው መልካም አባት መሆን እንደሚፈልጉ በቁጭትና በፍቅር ገልጸዋል።
ኬር ስታርመር የሌበር ፓርቲ አዲስ መሪ እስከሚመርጥ ድረስ በኃላፊነታቸው ላይ የሚቆዩ ሲሆን የፓርቲው የበላይ አካል ይህንን ምርጫ ፓርላማው በፈረንጆቹ መስከረም ወር ከመመለሱ በፊት እንዲያጠናቅቅ ጠይቀዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሊተኩ ይችላሉ ተብለው ከሚጠበቁት መካከል አንዱ የሆኑት አንዲ በርንሃም ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የአጋማሽ ምርጫ የማከርፊልድ ተወካይ ሆነው ማሸነፋቸውን ተከትሎ የፓርላማ አባልነታቸውን ሙሉዕ ለማድረግ ቃለ መሐላ ለመፈጸም በዌስትሚኒስተር እንደሚገኙ ታውቋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.