2ኛ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በባሌ ተከፈተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ባሌ ሮቤ— በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት 2ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ – የቱሪዝም እና ሆስፒታሊቲ ትምህርትን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ( AI ) በአዲስ እሳቤ ማላቅ – ( የወደፊት ክህሎቶችን፣ የፈጠራ አቅምንና እና ሥነ ምግባራዊ ሰው – ተኮር አሰራርን ማጎልበት ) ” በሚል መሪ ሃሳብ ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የመጡ ተናጋሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን እና ተሳታፊዎች በተገኙበት ሁለተኛው ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

የኮንፈረንሱ አስተናጋጅ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና (PhD) የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም የምንኖርበት ዘመን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በማሽን ትምህርት (Machine Learning) እና በአውቶሜሽን ምክንያት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር እየታየበት ያለና የሆስፒታሊቲውን ዘርፍ ሙሉ በሙሉ እየቀየረው የሚገኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኮንፈረንሱ አስተናጋጅ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና (PhD) የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ በንግግራቸውም የምንኖርበት ዘመን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በማሽን ትምህርት (Machine Learning) እና በአውቶሜሽን ምክንያት ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር እየታየበት ያለና የሆስፒታሊቲውን ዘርፍ ሙሉ በሙሉ እየቀየረው የሚገኝ መሆኑን ጠቁመዋል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብርሃነመስቀል ጠና አያይዘውም፣ ቴክኖሎጂው ሰብአዊ እሴቶችን፣ የሰዎችን ግላዊነት፣ ፍትሃዊነትንና ባህልን በጠበቀ መልኩ ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበትና ተማሪዎችንም ለነገው ያልተፈጠሩ የሥራ ዕድሎች በዲጂታል ክህሎትና በሰብአዊ እሴቶች ማነጽ እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተዋል።

የባሌን ምድር አንድ ፓርክ፣ ብዙ ዓለማት” ሲሉ የገለጹት ዶ/ር ብርሃነመስቀል፣ እንደ ባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የሶፍ ዑመር ዋሻ፣ የቱሉ ዲምቱ ጫፍ እና የዲሬ ሸኽ ሁሴን መካነ መቃብር ያሉ የተፈጥሮና የታሪክ ጸጋዎች መገኛ የሆነው ይህ ቀጠና ለዩኒቨርሲቲው ትልቅ ሕያው የመማሪያ ክፍል መሆኑንና የዩኒቨርሲቲውም ስኬት የሚለካው በምርምር ወረቀቶች ብቻ ሳይሆን በማኅበረሰቡ ውስጥ በሚያመጣው እውነተኛ ለውጥ መሆኑን አስታውቀዋል።

ከዚሁ የኮንፈረንስ መክፈቻ ጎን ለጎን፣ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከዩናይትድ ኪንግደም (UK) የመጡ የባለሙያዎች ቡድን በቅርብ ትብብር ያበለጸገውንና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀውን አዲሱን የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ (Website) በይፋ መርቋል።

ይህ አዲስ ዲጂታል መድረክ ዩኒቨርሲቲው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተደራሽነትና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር የሽርክና ውጤት መሆኑ ተገልጿል።

ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ምክትል አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ሌሊሳ ጫላ እና አቶ ሙሉጌታ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና መሪነት ፕሬዝዳንቱ የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ የባለሙያዎቹ ቡድንና ጥሪ የተደረገላቸው ክብራን እንግዶች መድረክ ላይ በመውጣት ድረ-ገጹን በጋራ እንድሚርቁ አድርገዋል።

በመጨረሻም፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ለሁለት ቀናት የሚቆየውን ይህንን ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በይፋ የከፈቱ ሲሆን፣ በቆይታውም ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመጡ ምሁራን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ከቱሪዝም ልማት ጋር ያገናዘቡ በርካታ የምርምር ሥራዎችና ውይይቶች እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።

በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የዩኒቨርሲቲው የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር እና የዕለቱ ቁልፍ ተናጋሪ ክቡር ዶ/ር አብርሃም በላይ፣ የቱሪዝም ስቴት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር እንደገና አበበ፣ የባሌ ዞን አስተዳደር ዋና አዛዥ ክቡር አቶ አብዱልሀኪም አሊዪ እና የባሌ-ሮቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ዲኖ አሚን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከአውሮፓ፣ ከእስያ፣ ከአፍሪካና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ በርካታ ምሁራን፣ ተመራማሪዎች፣ የዘርፉ የልማት አጋሮች እና ስፖንሰሮች በአካልና በበይነ-መረብ (ኦንላይን) በጋራ እየታደሙ ናቸው።

#MaddaWalabuUniversity #AI #Tourism #Hospitality #Conference #Robe #EthiopiaNews #Education #Innovation #MWU






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: