“MMA” ውድድር ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር ጥምረት ፈጠረ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​በኢትዮጵያ ታሪክ በከፍተኛ ዝግጅት የሚካሄደው ግዙፉ የ”MMA” (Mixed Martial Arts) ውድድር፣ ለስኬታማነቱ ከኩሪፍቱ ሪዞርት ጋር ዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም ስትራቴጂያዊ የትብብር ስምምነት ተፈራርሟል።

​የMMA ውድድር ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። ውድድሩ በሀገሪቱ የቱሪዝም እና የመዝናኛ ዘርፍ አቅም ላይ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ተፅዕኖ በመገንዘብ፣ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

በስምምነቱ መሰረት ተወዳዳሪዎች ለ1 ወር በኩሪፍቱ ቆይታ የሚያደርጉ ሲሆን ስምምነቱ ለአንድ አመት እንደሚቆይ ተነግሯል።

​ስምምነቱ የMMA ተወዳዳሪዎች በኩሪፍቱ ሪዞርቶች ልዩ ቅናሾችን እንዲያገኙ የሚያስችል ሲሆን፣ በጋራ የጤና እና ደህንነት ፕሮግራሞችን፣ ሀገራዊ የጤና ንቅናቄዎችን እና የተለያዩ ስፖርታዊ ኩነቶችን ለማዘጋጀት መንገድ ይከፍታል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: