ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን በመያዣነት በመጠቀም ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የጠየቁ ሦስት ፓኪስታናውያን በ

- Advertisement -
Sidebar AD

ለጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የውጭ ሀገር ዜጎችን በመያዣነት በመጠቀም ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የጠየቁ ሦስት ፓኪስታናውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ።
***
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የፓኪስታን ዜግነት ያላቸው ዝሻን ካሊድ፣ ፍርዝ መሃመድ እና መሀመድ ጀናይድ የተባሉ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሰኔ 4 እና ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ/ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ አትሌቶች መንደር ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በተከራዩት የመኖሪያ ቤት ውስጥ የህንድና የባንግላዴሽ ዜግነት ያላቸውን ግለሰቦች በመያዣነት በመጠቀም የግል ተበዳዮችን በገመድ በማሰርና በፕላስተር በማፈን ከ15 እስከ 30 ሚሊየን ብር በመጠየቅ ጥቃት አድርሰውባቸዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በዚህ ብቻ ሳያበቁ ሰኔ 11ቀን 2018 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት የገቡ 4 የህንድ ዜጎችን በማሰርና በመደብደብ ከ15 እስከ 25 ሺህ የህንድ ሩፒ አስልኩ በማለት ድብደባ ሲፈጽሙባቸው እንደነበር የግል ተበዳዮች ለፖሊስ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የወንጀሉ መፈጸም መረጃ የደረሠው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ተገቢውን የፍርድ ቤት መያዣና የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት ባከናወነው ኦፕሬሽን ተጠርጣሪዎቹን ለወንጀል ድርጊት ሲጠቀሙበት ከነበረው ቢላዋ፣ ገመድና ፕላስተር እንዲሁም ከተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርጣሪዎቹ እንዲያዙ መረጃ በመስጠት ላደረጉት ቀና ትብብር ምስጋናውን ያቀረበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙም ለፖሊስ መረጃ መስጠት እንደሚገባም መልዕክቱን አስተላልፏል።






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: